2010-04-17 09:22:23

በጤና ጥበቃ ጣቢያዎች የሚገኙት የጸሎት ቤት መሪዎች ካህናት


የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አዘጋጅነት የጤና ጥበቃ ጣቢያዎች በሚገኙት የካቶሊክ ቤተ ጸሎት መሪዎች ካህናት በጋራ ቅዱስ ዣን ማሪ ቪያነይ በሕይወት ዘመኑ RealAudioMP3 የኖረበት በፈረንሳይ ወደ ምትገኘው ኩራቶ ዳርስ ከተማ እና እንዲሁም ማርያም ለቅድስት በርናርደት የተገለጸችበት ሉርድን መንፈሳዊ ንግደት ለመፈጸም ወደ ፈረንሳይ መሄዳቸው ተገልጠዋል።

በዚህ እፊታችን ሰኞ የሚጠናቀቀው መንፈሳዊ ንግደት ተሳታፎዎች ካህናትን የመሩት የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዝይግሙንድ ዞሞውስኪ እና ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ኾሰ ረድራዶ መሆናቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ መንፈሳዊ ንግደት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የጤና ባለ ሙያዎች የሚንከባከበው ድርገት ሊቀ መንበር የኦዚየሪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሰርጆ ፒንቶር እንዲሁም የስነ ማሪያማዊ ጥናት ሊቅ አባ ስቴፋኖ ፊዮረስ እየተሳተፉ መሆናቸው ተገልጠዋል።

በዚህ አጋጣሚም ብፁዕ አቡነ ዞሞውስኪ ትላትና በሰጡት ጋዜጣዊ መገልጫ መንፍሳዊው ንግደት የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተመሠረተበት 25ኛው ዓመት መሠረት እና ዘንድሮ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዋጅ መሠረት በመታሰብ ላይ ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት መሆኑ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.