2010-04-17 09:21:01

ሐዋርያዊ ግብርረ ኖልዎ፣ በብሔራዊ እና በአለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያዎች


በኢጣሊያ ሎረቶ ከተማ በተለያዩ የዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ የካቶሊክ ጸሎት ቤት የግብረ ኖልዎ ተጠሪዎች ካህናት 14ኛው ጉባኤ ከባለፈው እሁድ ጀምሮ ሲካሄድ መቆየቱ የሚዘከር ሲሆን፣ ተገባእያኑ ትላትና ከቅዱስ አባታችን RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር በመገናኘት መሪ ቃል እና ቡራኬን በመቀበል ስብሰባውን ማጠናቀቃቸው ተገልጠዋል።

ስብሰባውን የጠራው የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሲሆን፣ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ ስለ ተካሄደው ስብሰባ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሰው ልጅ ተጓዥ ነው፣ በክርስትያናዊ አገላለጥ የሰው ልጅ ወደ እግዚአብሔር የሚጓዝ ፍጡር ነው፣ ስለዚህ ይህ የተካሄደው ስብሰባ ከዚህ ክርስትያናዊ አገላለጥ በመንደርደር በተለያዩ ዓለም አቀፍ እኛ ብሔራዊ አቀፍ የአሮፕላን ማረፊያዎች የሚለከተውን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በመተንተን፣ ቤተ ክርስትያን በሁሉም ሥፍራ ተገኝታ ለተጓዦች የምትሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከሁኔታው አንጻር ጋር በማዛመድ የሰውን ልጅ የሚፈጽመው ምድራዊው ጉዞውን ትሸኛለች ትርጉም እንዳለው ትመሰክራለች፣ በዚሁ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩት ካህናት ሊከተሉት የሚገባው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለይታም በማሳወቅ፣ በዚህ ተልእኮ የተሰማሩት ካህናት መካከልም መተዋወቅ እና የአግልግሎት ልምድ ልውውጥ እንዲኖር ያገዘ ስብሰባ ነበር ብለዋል።

ይህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ 1995 ዓ.ም. ለዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያተኮረ መመሪያ የወጠነው መመሪያ ከ 15 ዓመት በኋላ በመከለስ፣ ለሁሉም የካቶሊክ ቤት ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት እንዲደርስ በስብሰባው መወሰኑ አስታውቀው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.