2010-04-17 09:16:54

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ የመጽሓፍ ቅዱስ ድርገት አባላት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያ ቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ጸሎት የመጽሓፍ ቅዱስ ድርገት አባላት ጋር መርተው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ነጻነትን RealAudioMP3 በሙላት መኖር እና ኅሊናን በመጻረር ተመሳስሎ መኖር ለሚለው አባገነናዊው ወቅታዊው ባህል እምቢ እንዲል የሚያነቃቃ መሆኑ በማሥመር፣ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ቀዳሚ መሆኑም ቅዱስ ጴጥሮስ ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝን ያስፈልጋል ያለው እንደሚያረጋገጥልን በማብራራት፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ነጻነቱን እንዲጎናጸፍ እና እንዲኖር በወቅቱ ለነበሩት የሃይማኖት መሪዎች ትእዛዝ እምቢ ብሎ እራሱ ሆኖ ለመኖር ያበቃው ውሳኔ ነው በማለት፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም ሶቅርጠስ በአተኔ ፍርድ ቤት ፊት ቀርቦ እግዚአብሔር ለመሻት ተያይዞት የነበረው ፍልስፍናዊ ምርምር ካቋረጠ ነጻ እንደሚባል፣ ካልሆነ ግን ሞት እንደሚበየንበት ከዳኞች የቀረበበት አማራጭ በማጤን እውነተኛው ነጻነት ለመኖር በመፈለግም እግዚአብሔርን ለመሻት የተያያዘው ፍልስፍናዊ ምርምር እንደማያቋርጥ ማሳወቁ አስታውሰው፣ እውነተኛው ነጻነት ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ የሚገኝ ነው። በዚህ በምንኖርበት ዘመን የሰውን ልጅ ለእግዚአብሔርን ከመታዘዝ ነጻ ለማውጣት እየተባለ የተለያዩ ሥነ ሐሳቦች ተነድፈው ይነዛሉ፣ ይህ ስነ ሐሳብ በሥነ ኅላዌ ትንተና ሐሰት ነው፣ ምክንያቱን የሰው ልጅ በገዛ ራሱ የገዛ ራሱ ከገዛ ራሱ ኅልውና የሌለው በመሆኑም ነው። እግዚአብሔር የለም ወይንም በሰው ልጅ ሊደረስ የሚቻል ኅልው አይደለም ከተባለ በእግዚአብሔር ላይ የሚጸናው እምነት በሐሰት ላይ የጸና የአብላጫው የስምምነት ሐሳብ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። እንዲህ ከሆነ ከአብላጨው ውጭ የሚገኙት አናሳው የኅብረተሰብ አባላት የሚያንበረክክ አመለካከት እና እንዲታዘዙትም የሚያስገድድ ይሆናል። በክፋት ላይ የጸና የአብላጫ ስምምነት በኅብረተሰብ ዘንድ መታየቱንም ታሪክ ይመሰክረዋል። ይህ የሐሰት መንገድም የሰው ልጅ ራስ ገዝ እንዲሆን እንጂ ነጻነቱን አያረጋግጥለትም ብለዋል።

በአለም ታሪክ የታየው የናዚው አምባገነናዊ ሥርዓት፣ የማርክሲዝም ሥርዓት ጭምር የተመለከትን እንደሆነ፣ የፖሊቲካ ርእዮት ካጸናው የበላይ ሥልጣን በላይ የሆነ እግዚአብሔር የለም የሚሉ ናቸው። በዚያኑ ወቅትም እግዚአብሔርን አውቀው ሰማዕትነት የተቀበሉ ብዙ ናቸው፣ እግዚአብሔርን መምረጥ እና ለእርሱ መታዘዝ ዘወትር ወደኛ የመጣው የክርስቶስ ነጻ መወጣት እና ነጻነት ያረጋግጥልናል።

ሁሉም እንደሚያስቡት ማሰብ፣ በሚስማሙበት መስማማት የሚለው ጸረ ኅሊና ኅልዮ በጣም በተራቀቀ ስልትም በቤተ ክርስትያን ዘንድ ሊታይ የሚችል አምባገነናዊ ስነ ሐሳብ እንዳለም ዘክረው፣ በዚህ አንጻር ብዙዎቻችን ይላሉ ቅዱስ አባታችን፣ የሕይወት ፍጻሜ የሆነው ስለ ዘለዓለማዊ ሕይወት ጉዳይ እና በዚህ ላይ የጸናው የሕይወት መመዘኛዎች በተመለከተ ከመናገር እና ከመመስከር እንቆጠባለን፣ በጣም ኃይለኛ እና የሚያስፈራ መስሎ ስለሚታየን ንስሓ የሚለውን ቃል በማግለልም የክርስትናውን ሕይወታችንን እንኖራለን፣ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት የወሲብ አመጽ አማካኝነትም ከብዙዎች እየተሰነዘረብን ያለው ወቀሳ እና ክስ ንስሓ መግባት እንዳለብን እና በክርስትናው ሕይወታቸው ይህ ሚሥጢር አቢይ ትርጉም እንዳለው የሚያሳስበን አወንታዊ ተግባር አድርገን መመልከት ይኖርብናል ብለዋል።

እየተሰነዘረብን ያለው ወቀሳ እና ክስ ስቃይ እያስከተለብን ቢሆንም ቅሉ፣ ተጸጽቶ እና አዝኖ እራስን ለማንጻት በእግዚአብሔር ለመለወጥ መፍቀድ እንዳለብን የሚያሳስበን ከስቃይ የሚገኝ ጸጋ ነው ምክንያቱም መንጻት እና ኅዳሴ የመልኮታዊ ምኅረት ሥራ ነው ካሉ በኋላ የሰጡትን ስብከት ሕይወታችን እውነተኛ ሕይወት ዘለዓለማዊ ሕይወት የፍቅር እና የእውነት ሕይወት እንዲሆን እንጸልይ በማለት ማጠቃለላቸው ከቅድስት መንበር የተላለፈልን መግለጫ ያመለክታል።
All the contents on this site are copyrighted ©.