Home Archivio
2010-04-14 14:10:49
የፍትሃት ቅዳሴ፣ በስሞሎንስኪ በአይሮፕላን አደጋ ምክንያት ለሞቱት
የካቶሊክ ትምህርት የሚንከባከበው ቅዱስ ማህበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዜኖን ግሮቾለውስኪ የመሩት የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ፣
ጳጳሳዊ የጤና ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ሊቅ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዞሞውስኪ እና ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ኾሴ ልዊስ ማርኪተ ሬድራዶ እና ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ አስፈጻሚ ጳጳሳዊ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፒየሮ ማሪኒ እና ከመቶ በላይ የሚገመቱ ካህናት የተሳተፉበት በቅድስት መንበር የፖላንድ ልኡከ መንግሥት ሃና ሱቾካ እና ሌሎች ልኡካነ መንግሥታት የተሳተፉበት በአይሮፕላን አደጋ ሳቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩ ለፖላንድ ርእሰ ብሔር ሌኽ ካዝይንስኪ እና ለክብርት ባለ ቤታቸው ማሪያ እና ሌሎች የአደጋው ሰለባ ለሆኑት ትላንትና ሮማ በሚገኘው በቅዱስ መንፈስ ዘ ሳሲያ የፍትሃት ቅዳሴ መቅረቡ ተገለጠ።
የደረሰው አሰቃቂው አደጋ በማስመልከትም ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዚሞውስኪ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሞታችንን ሞቶ ከሞት እርዛት ነጻ ያወጣን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፖላንድ ህዝብ፣ ለሟቾች ቤተ ሰብ ማጽናናቱን ይሰጥ ዘንድ እና ለሞት አደጋ የተጋለጡትም እግዚአብሔር በመንግሥቱ ይቀበላቸው ዘንድ መጸለዩንም ገልጠው፣ ሁላችን የትንስኤውን እምነት ካለ ማመንታት መኖር ይገባናል፣ ይህች የር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አገር እግዚአብሔር ይባርካት በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.