2010-04-14 14:16:08

የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፣ ኅዳሴ ትምህርተ ክርስቶስ


በአሁኑ ዘመን በመስፋፋት ላይ ያለውን የግለኝነት እና የግድ የለሽነት የእሰቶች ደረጃ ብሎ የለም ማመን አለ ማመን ያው ነው የሚለው ተዛማጅ ባህል እግምት ውስጥ በማስገባት የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 ስለ ኅዳሴ ትምህርተ ክርስቶስ ጉዳይ የሚያመለክት ሰነድ ለሁሉም ቁምስናዎች ማስተላለፉ ተገለስጠ። በነዚህ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ በየወቅቱ እየታደሰ ይቀርብ የነበረው ትምህርተ ክርስቶስ ዳግም ወቅታዊውን ባህል እግምት ውስጥ በማስገባት አስፍሆተ ወንጌል እና ትምህርተ ክርስቶስ ለክርስትያናዊ ሕይወት በሚል ርእስ ሥር የቀረበ ሰነድ መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች የጠለቀ ሕንጸት እንዲያገኙ እና ስለ ቤተ ክርስትያን ታሪክ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የቲዮሎጊያ-ፍልስፍና ሕንጸት እንዲያገኙ የሚያነቃቃ ሰነድ መሆኑን ለማወቅ ሲቻል፣ ሰነዱ የኢጣሊያ ወቅታዊው ባህል፣ ኅብረ ባህል ኅብረ ሃይማኖት የመሳሰሉትን ማኅበራዊ ጉዳይ እግምት ውስጥ ያስገባ፣ ክርስትያኖች ክርስትያናዊ ሕይወታቸው እንዲያጠነክሩ የተጠሩ መሆናቸውም የሚያሳስብ ለእምነት የሚያበረታታም መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.