2010-04-14 14:07:29

የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት በቅድስት መንበር


የካቶሊክ ጳጳሳት በያምስቱ ዓመት በቫቲካን ሓዋርይዊ ጉብኝት በማከናወን ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ውህደት ብሎም ለቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥነታቸውን፡ አንድነታቸውን ለመመስከር RealAudioMP3 የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለመሳለ ስለ ቤተክርስትያናቸው ወቅታዊ እና አንግብጋቢ ርእሶች አስደግፈው ከቅዱሱ ኣባታችን ጋር በመምከር መሪ ቃል የሚያገኙበት መንፈሳዊ ጉብኝት ምክንያት በብራዚል የኖርተ ዳግማዊ አወራጃ ብፁዓን ጳጳሳት በቫታካን እንደሚገኙ ተገለጠ። የነዚህ ብፁዓን ጳጳሳት የመጀመሪያው ቡድን ትላትና በካስተል ጋንደልፎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንጻ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የአባየተቱባ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍላቪዮ ጆቨናለ በዚህ አጋጣሚም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ኖርተ ዳግማዊ በብራዚል የአማዞን ምሥራቃዊ ክልል በሆነው በዚህ አውራጃ በጠቅላላ 14 ብፁዓን ጳጳሳት የሚገኙበት ሰፊ ክልል መሆኑ ገልጠው፣ ከህዝብ ብዛት አጻር ሲታይ የክህነት ጥሪ እጥረት እንዳለ እና አንድ ካህን 20 ሺሕ ምእመናን የሚሸፍን፣ በመልእክአ ምድር አቀማመጥም መሠረትም ቁምስናዎች እጅግ የተራራቁ፣ ባለው በካህናት እጥረት ሳቢያ የክልሉ ቅዱሳት ሚሥጢራትን ለማዳረስ እጅግ እንደሚያዳግታት ገልጠዋል። አንዳንድ የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን በዓመት ሁለቴ በዛ ከተባለም ሦስቴ ቅዳሴ እንደሚደርሳቸው በመግለጥ፣ ይኽ ችግር ለመወጣትም ቤተ ክርስትያን ዓለማውያን ምእመምናን ትምህርተ ክርስቶስ በማስተማር የእግዚአብሔር ቃል በማዳረስ ክርስትያኖችን በማነጽ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ረገድ ተሳታፊነታቸው እንዲያበረቱ በማድረግ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

በዚህ አጋጣሚም በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት የወሲብ አመጽ ምክንያት በቤተ ክርስትያን እና በቅዱስ አባታችን ላይ እየተነዛ ያለው አሉታዊ አስተያየት ሳይበግረን፣ የክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት ለቅዱስነታችን ትብብራቸውን እና ቅርበታቸውን በመመስከር ላይ ይገኛሉ ካሉ በኋላ፣ ቤተ ክርስትያን የዚህ ዓይነቱ አመጽ በማውገዝ ጨርሶ እንዲወገድ በሚደረገው ጥረት ቀዳሚው ሥፍራ ይዛ እንደምትገኝም አስታውሰው፣ አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት ወንጀል መላ ቤተ ክርስትያን ውሉደ ክህነት እና ቅዱስ አባታችንን ተጠያቂ አድርጎ መውቀሱ ተገቢ እይደለም፣ እያንዳንዱ በሚፈጽመው ግላዊ ተግባር ሊፈረድበት ይገባል። ቅዱስ አባታችን ባላቸው ኃላፊነት ጸንተው ሕዝበ እግዚአብሔርን እንዲመሩ እግዚአብሔር መርጧቸዋል፣ ስለዚህ በአሉ ባልታ ሳይበገሩ እግዚአብሔር በሚሰጣቸው ኃይል ይመሩ ዘንድ የክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት ቅርበታቸው እና ትብብራቸው ማረጋገጣቸው ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.