2010-04-14 14:11:48

ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ


ስለ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ እስካሁን ድረስ በፖለቲካ እና በስነ መስተዳድር ረገድ የተደገፉ ጥናቶች ብቻ ሲቀርብ መቆየቱ የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ ልዩ ውሳኔ መሠረት በቫቲካን RealAudioMP3 ዝግ ቤተ መዝገብ ዘንድ የሚገኘው የር.ሊ.ጳ. ፒቶስ 11ኛ ጉዳይ የሚያወሳ የተሟላው ሰነድ ክፍት እንዲሆን ከተደረገ በኋላ፣ ስለ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ ውሳኔዎች አስተምህሮ በጠቅላላ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ኃላፊነታቸው የፈጸሙት ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚያወሳ እንዲሁም እ.ኤ.አ.በ 2009 ዓ.ም. ጳጳሳዊ የስነ ታሪክ ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ ያዘጋጃቸው ስለ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጥናት ያቀረበው ሰነድ ጭምር በማመላከት፣ የዚሁ ጳጳሳዊ ኮሚቴ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኮሲሞ ሰመራሮ የደረሱት በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሐፍ ትላትና እዚህ በቫቲካን ሬዲዮ ሕንፃ በሚገኘው የጉሌልሞ የስብሰባ አዳራሽ ለንባብ መቅረቡ ተገልጠዋል። በዚህ አጋጣሚም ኣባ ሰመራሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ስለ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ ታሪክ እስካሁን ድረስ ስለ ያስተዳደር ስልታቸው የቫቲካን ከተማ ልኡላዊነት መመሥረት በቫቲካን እና በተለያዩ አገሮች መካከል ግኑኝነት ለማነቃቃት የሰጡት አስተዋጽኦ እና ፖሊቲካ እና ቅድስት መንበር በሚሉት ርእሶች ብቻ ብዙ ሲጻፍ ቆይተዋል፣ ይህ ጳጳሳዊ የስነ ታሪክ ኮሚቴ ጉዳዩን በመጤን የፒዮስ 11ኛ ሐዋርያዊ አገልግሎት ምን እንደሚመስል ለማሳወቅ፣ ልዩ ጥናት በማድረግ ያሳተመው መጽሓፍ መሆኑ አስረድተዋል።

በዚሁ በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ ዘመን የቤተ ክርስትያን ጥሪ በሚል ርእስ ሥር በተደረሰው መጽሐፍ የጥናት ጽሑፍ ያቀረቡት የስነ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ ሊቅ የቫቲካን ዝግ ቤተ መዝገብ ኅየንተ ብፁዕ አቡነ ሰርጆ ፓጋኖ በበኩላቸውም በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ የጴጥሮስ ተከታይ ኃላፊነት ሙላት ያለው ታሪክ ለማሳወቅ የሚያግዝ መጽሐፍ መሆኑ በማስረዳት፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመሆን ከተሸሙበት እ.ኤ.አ. ከ የካቲት 6 ቀን 1922 ዓ.ም. ጀርሞ ከዚህ ዓለም በሞት እስክ ተለዩበት የካቲት 10 ቀን 1939 ዓ.ም. በሳቸው ዘንድ የተመራቸው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ታሪክ በጥልቀት የሚያወሳ መጽሓፍ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.