2010-04-14 14:09:28

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 5ኛው ዓመት በመንበረ ጴጥሮስ ተልእኮ


ብፁዕ አቡነ ጂዮርግ ጋንስዋይን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለመንበረ ጴጥሮስ የተሾሙበትን 5ኛውን ዓመት ምክንያት የአምስቱ ዓመት ር.ሊ.ጳጳሳዊ ኃላፊነታቸውን የሚዳስስ በስእላዊ መገልጫ የተደገፈ በጀርመንኛ ቋንቋ RealAudioMP3 ደረሱት ጀርመን በሚገኘው የሄርደር ማተሚያ ቤት የታተመ መጽሐፍ ትላንትና ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ይህ መጽሐፍ ትላንትና የሄርደር ማተሚያ ቤት የቢልድ ዕለታዊ ጋዜጣ እና የቫቲካን ማተሚያ ቤት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ለቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በይፋ መቅረቡ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለመንበረ ጴጥሮስ በተሾሙበት በነዚህ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ያከናወኑዋቸው ሐዋርያዊ ተልእኮ የሚዳስ መጽሐፍ የጣልያንኛ ቋንቋ ትርጓሜው በቫቲካን ማተሚያ ቤት በኩል ለህትመት መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
All the contents on this site are copyrighted ©.