2010-04-13 11:48:48

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ሠራተኞች “እውነትን በፍቅር” የሚለውን የር.ሊ.ጳ መልዕክት አስመልክተው የአንድ ቀን ወርክሾፕ አካሄዱ


የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ሠራተኞች ሚያዝያ 4 ቀን 2002 ዓ.ም “እውነትን በፍቅር” የተሰኘውን የብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት አስመልክተው የአንድ ቀን ወርክሾፕ አካሂደዋል፡፡

በመልዕክቱ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት ክቡር አባ ዳንኤል አሰፋ የካፑቺን ፍራንሲስካውያን የፍልስፍናና ነገረመለኮት ተቋም ዳይሬክተር ናቸው፡፡

በወርክሾፑ ላይ ህገወጥ የሰው ልጆች ዝውውር፣ የሰው ልጅ ክብርና፣ ፍትህና ሰላም በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ መላው የጽ/ቤቱ ሠራተኞችም ተካፋይ ሆነዋል፡፡

ወርክሾፑ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት የፍትህና ሰላም ክፍል የተዘጋጀ ነበር፡፡








All the contents on this site are copyrighted ©.