2010-04-13 11:45:00

የርሊጳ በነዲክቶስ የቆጵሮስ ሐዋርያዊ መርሃ ዑደት ርሊጳ ይፋ ሁነዋል፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት አስራ ስድስተኛ ከሁለት ወራት በኃላ በምስራቃዊ መካከለኛው ምስራቅ ቆጵሮስ ሐዋርያዊ ዑደት እንደሚያደርጉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት ፡ፊታችን ሰነ ወር አራት ቀን ሞልታ ለመጐብኘት ርእሰ ከተማ ኒኮሲያ ይገባሉ ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቆጵሮስ እንደገቡ ፓፎስ ላይ በሚገኘው አግያ ኪርያኪ ቤተክርስትያን መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ መግለጫው በተጨማሪ ገለጠዋል።

በነገታው ኒኮሲያ ላይ ከደሴቲቱ ፕረሲዳንት ከዲፕሎማቶች ከካቶሊካዊ ማኅበረ ስበ ጋር በመገኛኘት እንደሚነጋገሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።

ከቀትር በኃላም ከየቆጵሮስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ ክሪስቶሞስ ዳግማዊ ጋር እንደሚገናኙ ተመልክተዋል።

ከሰዓት በኃላም በቆጵሮስ ኒኮሲያ ላይ ለጥቅላላ ካቶሊካውያን መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ

ተገልጠዋል።

ሰንበት ሰነ ስድስት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ኒኮሲያ የመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት ጉባኤ መመርያ ሰነድ ኅትመት መሠረት በማድረግ ኒኮሲያ ላይ በሚገኘው ስታድየም መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ እና ከቀትር በኃላም እዚያው የሚገኘው የማሮናውያን ካተድራል እንደሚጐበኙ የቆጵሮስ ሐዋራያዊ ዑደታቸው መርሃ ግብር አስገንዝበዋል። ከቅተር በኃላም ውደ ሐዋርያዊ መንበራቸው እንደሚመለሱ ተያይዞ ተገልጠዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከቆጵሮስ በፊት ፊታችን ቅዳሜ በሞልታ ሐዋርያዊ ግብኝት ለማካሄድ ፊታችን ቅዳሜ ከቫቲካን እንደሚነሱ የሚታወስ ሲሆን፡ ይህ ምክንያት በማድረግ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ለሃገሪቱ ምእመናን ሐዋርያዊ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ሐዋርያዊ መልእክቱ የሞልታ ደሴት ታሪኽ ከ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ጋር የተሳሳሰረ መሆኑ እና የሞልታ ምእመናን ሐዋርያ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ የሰጠውን ብስራት እንዲመሰክሩ መጠራታቸው መሳሳሰቡ ተመልክተዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሞልታ ሐዋርያዊ ጉብኝት የሀገሪቱ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የመንፈሳዊ ተሐድሶ ቀስቃሽ መሆኑ መልእክቱ ማመልከቱ መግለጫው አስገንዝበዋል።

የሞልታ ጳጳሳት በበኩላቸው የሰጡት ሐዋርያዊ መልእክት እንዳመልከተው ፡ ሐዋርያ ጳውሎስ በደሴታችን ባሕር ላይ የሰጠመው እንዳጋጣሚ አይደለም እና የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ሐዋርያዊ ጉብኝት በጉጉት እንተባበቃለን በማልት ምስገንዘቡ ተነግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ፡የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ የቺለ ጉብኝት ባለበት እየቀጠለ መሆኑ ይታወቃል።

ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ የተለያዩ የቺለ ክልሎች እየተዘዋወሩ በመጐብኘት ላይ መሆናቸው ከሀገሪቱ የቤተ ክርስትያን እና ሲቪል ማኅበረሰቦች እተገናኙ እየተወያዩ መሆናቸው ተገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.