2010-04-13 12:03:27

ዓመታዊ በዓለ መለኮታዊ ምህረተ


ከበዓለ ፋሲካ ሳምንተ ቀጥሎ የሚውለው እሁድ የመለኮታዊ ምህረት በዓል ተብሎ እንዲከበር እ.ኤ.አ. በ 1930 ዓ.ም. እናቴ ቅድስት ፋውስቲና ክዋልስካ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበሉት መልእክት ምክንያት ትላትና የላቲን ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የመለኮትዊ ምህረት በዓል አክብራ ውላለች።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ እዚህ በሮማ የመለኮታዊ ምህረት ባዚሊካ አስተዳዳሪ አባ ጆሴፍ ባርት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቅድስት ፋውስቲና ኮዋልስካ አቢይ መንፈሳዊ ተልእኮ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ምህረት መመስከር እና የሰው ልጅ የመለኮታዊ ምህረት ፈላጊ ይኸንን ምህረት የሚጠማ መሆኑ እና መለኮታዊ ምህረት ድካምነት ሳይሆን መለኮታዊ ኃይል መሆኑ የሚከበርበት ዕለት ነው ካሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር በክፋት መንፈስ ላይ ድል የነሳበት ክብረ በዓል ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ክርስትያኖች በሞት ላይ ድል የነሳው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች ናቸው በማለት የሰጡትን አስተምህሮ የሚያጎላ እለት መሆኑም አባ ባርት አብራርተው፣ ቅድስት እናቴ ፋውስቲና በመንፈሳዊው ማህደራቸው ዘንድ መለኮታዊ ምህረት በመንፈሴ ላይ የታተመ እቅድ ነው፣ ሁሉም ኃጢአተኛ መሆኑ ሳያስፈራው ከመሐሪው አባቱ ጋር ለመወያየት እና ምህረት በመጠየቅ እውነትን ለማወቅ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት መንገድ የሚያሳየን የእግዚአብሔር ምህረት ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዳችን የዚህ መለኮታዊ ምህረት ተካፋዮች እና አብሳሪዎች መሆናችን የሚያሳስብ እለት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.