2010-04-13 11:45:22

በኬንያ ፡ የሃይማኖትና የመንግስት መሪዎች መካከል ውይይት መካሄዱ፡


የኬንያ አብያተ ክርስትያናት መሪዎች እና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሃገሪቱ ሕገ መንግስት ማሻሻያ ሰነድ በተመለከተ መወያየታቸው እና ስምምነት ላይ ለመድረስ አለመቻላቸው ደይሊ ኔሽን የተባለ ጋዜጣ አስታውቀዋል።

በዚሁ የኬንያ ሕገ መንግስት ረቂቅ ትኩረት የሰጠ ግንኙነት የኬንያ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጆን ንጁወ የካካመጋ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍሊፕ ሳሉመቲ የኬንያ አብያተ ክርስትያናት ሊቀ መንበር እና ዋና ጽሐፊ ቄስ ቻርለስ ኪቢኮ እና ፒተር ካንያጃ የተገኙ ሲሆን በመንግስት በኩል ፕረሲዳንት ምዋይ ኪባኪ እና ረዳት ፕረሲዳንት ካሎንጾ ሙስዮካ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መገኘታቸው ዳይሊ ነሽን አመልክተዋል።

በዚሁ የኬንያ የአብያተ ክርስትያናት እና የመንግስት ከፈተኛ ባለስልጣናት ግንኙነት ረቂቅ ሕገ መንግስቱ የሰው ከመጸነስ እስከ ተፈጥሮአዊ ሞት የመኖር መብት እንዲጠበቅ ካድሂ የተባለው የእስላሞች ፍርድ ቤት የሃይማኖት ግጭት ሊቀስቅስ ስለ ሚችል እንዲገታ የሃይማኖት መሪዎች መጠየቃቸው ተነግረዋል። ረቂቅ ሕገ መንግስቱ በሀገሪቱ ፓርላማ እየተጠና መሆኑ የሚታወስ ነው። ደይሊ ኔሽን ዕለታዊ ጋዜጣ ከናይሮቢ እንዳመልከተው ፡ ሁለቱ ውገኖች ረቂቅ ሕገ መንግስቱ በተመለከተ ቀጣይ ውይይት ለማድረግ እና አንድ ተቸባጭ ስምምነት ላይ ለመድረስ በስምንት ሰዎች የቆመ ያጋራ ኮሚስዮን መስርተዋል።

ፊታችን ሐምለ ወር ላይ ረቂቅ ሕገ መንግስቱ በተመለከተ ሀገሪቱ ውስጥ ረፈረንደም ውሳኔ ህዝብ እንዲሰጥ እቅድ እንዳለ የሚታወስ ሲሆን የኬናይ አብያተ ክርስትያናት መሪዎች ረፈረንድሙ ለስሶት ወራት እንዲተላለፍ መጠየቃቸው ተያይዞ ተገልጠዋል።

በሚቀጥለው ቅርብ ግዜም የመንግስት እና የሀገሪቱ የእስላም ሃይምኖት መሪዎች ተገኛንተው ረቂቅ ሕገ መንግስቱ በተመልከተ እንደሚወያዩ ደይሊ ኔሽን አስታውቀዋል።

የኬንያ ረቂቅ ሕገ መንግስት ህዝብ እና የሃይማኖት መሪዎች በሚስማሙበት አኳን እንደሚቀየስ የመንግስት ቃል አቀባይ መግለጣቸውም ተያይዞ ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.