2010-04-13 11:46:02

በኢትዮጵያ ዓድዋ ላይ አዲስ ሕክምና ቤት ስራ እቅድ


በስሜናዊ ኢትዮጵያ ዓድዋ ከተማ ላይ የኪዳነ ምሕረት ሕክምና ቤት በሚሰራበት ቦታ መሠረተ ድንጋይ እንደተቀመጠበት ከቦታው የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

ሕክምና ቤቱ ሲጠናቀቅ አንድ ሃያ ስምንት ሕሙማን ለምስተናገድ ችሎታ ያለው የመጅመርያ ርዳታ ሕክምና የሚሰጥ የተለያዩ በሽታዎች ለመፈወስ ዝግጁ ሆኖ እንደሚቀርብ ዜናው አመልክተዋል። አጠገቡም ኔርሶች የሚማሩባቸው እና የሚሩባቸው ቤቶች እንደሚሰሩም ተያይዞ ተገልጠዋል።

እዚያው ዓድዋ ከተማ ላይ ለሀገር ሐኪሞች ከፍተኛ የሕክምና ተምህርት እንደሚሰጥም ከቦታው የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

በዚሁ ሕክምና ቤት የሚሰራበት ቦታ መሠረተ ድንጋይ ሲጣል በርካታ የሃይማኖት የመንግስት እና የሲቪክ ከፍተኛ ባለስልጣናትመገኘታቸው ከቦታው የመጣ ዜና ገልጸዋል።

ቶሎ ተሰርቶ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚጠበቀው ሆስፒታሉ በዓድዋ እና አከባቢ የሚኖረው ከአንድ ሚልዮን ለሚበልጥ ህዝብ የሕክምና እገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተወስተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.