2010-04-13 11:45:41

በሱዳን ህዝባዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው ፡


በሱዳን ትናንትና የጀመረው ፕረሲዳንታዊ እና ፓርላመንታዊ ምርጫ እንደቀጠለ መሆኑ ከካርቱም ተመልክተዋል።

በሃያ አረታ ዓመታት የብዙኀን ፓርቲዎች ነጻ ምርጫ ሲካሄድ ይህ የመጀመርያ ግዜ እንደሆነ የሚታወስ ሲሆን የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕረሲዳንት ጂሚ ካርተር ጨምሮ ከአስራ ስምንት ሀገራት የተውጣጡ ስምንት መቶ ታዛቢዎች የምርጫው ሁኔታ እየተከታተሉ መሆናቸው ተመልክተዋል።

ጂሚ ካርተር ምርጫው እስከ ዛሬ ድረስ በትክክለኛ መንገድ እየተካሄደ መሆኑ ዛሬ ጥዋት ካርቱም ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁ ህዝባዊ ፕረሲዳንታዊ እና ፓርላማነታዊ ምርጫ አስራ ስድስት ሚልዮን ሱዳናውያን የምርጫው ተሳታፊ እንዲሆኑ እንደሚጠበቁ ተገልጸዋል።

በመጀመርያ አስራ ሁለት ለፕረሲዳታዊ ምርጫ ውድድር በእጩነት የቀረቡ ሲሆን አራቱ ከውድድሩበመውጣቸው ስምንት እየወዳደሩ መሆናቸው ይታወቃል።

የሱዳን ፕረሲዳንታዊ እና ፓርላመንታዊ ኮሚሽን የምርጫው ግዜ በአምስት ቀናት ሳይራዘም እንደማቀር ካርቱም ላይ መግለጹ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል ።

በሰሜናዊ ምዕራባዊ ሱዳን ዳርፉር ላይ ባለው ፖሊካዊ ሁከት ምርጫ እንደማይካሄድ ቀደም ሲል ተገልጦ ነበር ።








All the contents on this site are copyrighted ©.