2010-04-13 11:59:07

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.  በነዲክቶስ 16ኛ፣ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ አቢይ የፍቅር መምህር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ዓርብ በካስተል ጋንደልፎ ስለ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ሕይወት ታሪክ በማስደገፍ የተቀረጸው ፊልም መከታተላቸው ሲገለጥ፣ ይህ ከሮማው ሰማይ በታች በሚል ርእስ ሥር የተደረሰው ፊልም ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ እ.ኤ.አ. ከ 1943 ዓ.ም. እስከ 1944 ዓ.ም. የፋሺስት ናዚው ሥርዓት ያረማምደው በነበረው ጸረ ሴማዊ ፖለቲካ መሠረት ስደት እና መከራ ብሎም ሞት ይደርስባቸው ለነበሩት የአይሁድ እምነት ተከታይ ዜጎች ለማዳን የፈጸሙት ግብረ ሰናይ የሚያወሳ ሲሆን፣ ይህ ፊልም በኢጣሊያ ራይ ኡኖ በሚል መጠሪያ በሚታወቀው የቴሌቪዥን ታጣቢያ አማካኝነት መሰራጨቱ ሲታወቅ፣ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፊልሙን ቀድመው ከተከታተሉ በኋላ የር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ግብረ ሰናይ እጅግ ማድነቃቸው እና የፍቅር እና የእምነት እንዲሁም የተስፋ አቢይ መምህር መሆናቸው የመሰከረ ፊልም ነው እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

የናዚ ወታደሮች ሮማ የሚገኙት የአይሁድ እምነት ተከታይ የኢጣሊያ ዜጎችን ለማሳደድ እና ለሞት ለመዳረግ ሁለት መቶ ሕፃናት የሚገኙባቸው በጠቅላላ አንድ ሺሕ የሚገመቱትን በማፈስ ጀርመን ወደ ሚገኘው የአይሁድ እምነት ተከታዮች ይታጎሩበት እና ለሞት ይዳረጉበት ወደ ነበረው የአውሺውዥ የእልቂት ሠፈር ለማዛወር የፈጸሙት የጭካኔ ተግባር በመቃወም እነዚህን የአይሁድ እምነት ተከታዮችን ለማዳን ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ የፈጸሙት አቢይ የፍቅር ሥራ የሚተርክ በተጨማሪም የኢጣሊያው የፋሺስት መንግሥት የናዚው ፖለቲካ ተከታይ በመሆን ያሳየው ጭካኔ የሚጻረር ተግባራቸው እና እ.ኤ.አ. ሰኔ 4 ቀን 1944 ዓ.ም. ሮማ ከናዚው ፋሺስታዊው መንግሥት ነጻ የወጣችበት ቀን የሚተርክ እና በዚያኑ የሰቆቃው ዓመታት ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ካለ መታከት እምነትን  በመመስከር ጥበብ በተካነው አንደበት ለሁሉም የእውነትን መንገድ በመጠቆም ያስተማሩ ለሞት እና ለስደት ይዳረጉ የነበሩትን የአይሁድ እምነት ተከታዮችን ለማዳን የፈጸሙት የፍቅር ሥራ የሚያወሳ እውነትን የሚገልጥ ፊልም ነው በማለት አስተያየት መስጠታቸው ተገልጠዋል። ግብረ ሰናይ የሁሉም ተግባር አመክንዮ መሆን አለበት የሚለው ሁሉን የሚያቀራርበው እሰይታ በር.ሊ.ጳ. ፕዮስ 12ኛ የተመሰከረው የፍቅር የእምነት እና የተስፋ ሥራ የሚያንጸባርቅ ነው እንዳሉ ለማውቀ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.