2010-04-10 10:09:38

የአሜሲያ (AMECEA) ጠቅላይ ጸሐፊ በኢትዮጵያ ሓዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው


ክቡር አባ ፓየስ የአሜሲያ ጠቅላይ ጸሐፊ በኢትዮጵያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ መጋቢት 29 ቀን 2002 ዓ.ም. አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ በተመሳሳይ ዕለት ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ጉብኝታቸውን የጀመሩ ሲሆን ማምሻውን ከብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስነ ሊቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡

ክቡርነታቸው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን በመቀጠል መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም ወደ መቂ ሃገረ ስብከት የተጓዙ ሲሆን በቀጣይም የሆሳዕናንና፣ የእምድብርን ሃገረስብከት የሚጎበኙ መሆኑ ታውቋል፡፡

ክቡር አባ ፓየስ በቅርቡ 25ኛ ዓመት የክህነት አገልግሎት በዓላቸውን ማክበራቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት

ማኅበራዊና ህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ








All the contents on this site are copyrighted ©.