2010-04-09 17:42:40

ቅዱስ መግነዝ ለትዕይንተ ህዝብ ይቀርባል፡


ነገ ሚያዝያ አስር ቀን እኤአ በሰሜናዊ ጣልያን ቶሪኖ ላይ በሚገኘው ጥንታዊ ካተድራል የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መግነዝ ለተዕይንተ ህዝብ እንደሚቀርብ የክልሉ ቤተክርስትያን የሰጠችው መግለጫ አስታውቅዋል።

ቅዱስ መግነዙ ከነገ ጀምሮ እስከ ፊታችን ግንቦት ወር ሃያ ሶስት ቀን እኤአ እንደሚቆይ መግለጫው በተጨማሪ አመልክተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ግንቦት ሁለት ቀን ላይ ወደ ቶሪኖ በመጓዝ ቅዱድስ መግነዙ ይታዘባሉ ከተማይቱ ላይም ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተያይዞ የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

በሁለት ሺ ዓመተ ምህረት እኤአ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መግነዝ ለትዕይንተ ህዝብ መቅረቡ የሚታወስ ነው።

ቶሪኖ ከተማ ላይ ከነገ ጀምሮ ለህዝብ የሚታየው ቅዱስ መግነዙ በሁለት ሚልዮን የሚገመት ህዝብ እንዲመለከተው የጠበቃል ሲል መግለጫው አክሎ አስገንዝጽበዋል።

የሀገረ ስብከቱ የቅዱስ መግነዝ ኮሚስዮን ሊቀ መንመንበር ብፁዕ አቡነ ጁሰፐ ጊበርቲ ሲገልጹ እንዳመለከቱት ቅዱስ መግነዙ ክርስቶስ ተሰቃይቶ መስቀል ላይ እንደሞተ የሚያስረዳ ነው።

ጨርቁ በርእግጥ ክርስቶስ የተገነዘበት ጨርቅ መሆኑ ውይም አለ መሆኑ የቤተክርስትያን አቋም ምን እንደሆነ የገረ ስብከቱ የቅዱስ መግነዝ ኮሚስዮን ሊቀ መንበር ብፁዕ ኣአቡነ ጁስፐ ጊበርቲ ሲመልሱ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በዚሁ ጉዳይ እጅግ ጥንቁቅ መሆንዋ ጠቅሰው ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅዱስ መግነዙ እንደተመልከቱት ኢየሱስ ክርስቶስ የተገነዘበት ጨርቅ መሆኑ እና አለመሆኑ ለሳይንስ ምርምር የሚተው መሆኑ መግለጣቸው አስታውሰው እስካሁን ድረስ የተካሄዱ ምርምሮች የክርስቶስ መግነዝ አለመሆኑ የተባለ ነገር እንደሌለ ገልጠው ፡ ጨርቁ እና ሐዋርያት ስለ ክርስቶስ ያሉ እና በቅዱስ መጽሐፍ የሰፈረውን እንደ ሚጣጣም ገልጸዋል።

ምርምሩ ቀጣይ መሆኑንም በሀገረ ስብከቱ የቅዱስ መግነዝ ኮሞስዮን ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጁሰፐ ጊበርቲ አም አልክተዋል።

ቅዱስ መግነዙ ደጋግመው የታዘቡት ብፁዕ አቡነ ጁሰፐ ጊበርቲ እንደገለጡት ፡ ቅዱስ መግነዙ ስትመለከተው በውስጥህ የዓቢይ የስሜት ስቃይ የሚቀስቅስ ሆኖ እኔ ክርስቶስ የተገነዘበት መሆን አለበት ብዪ ስለማምን እሱ ሰውን ክእኩይ ተግባር ለማዳን ብርሃን ለመስጠት ምን ያህል እንደተሰቃየ ለመረዳት ችያለሁኝ ሲሉ መግለጣቸው ታውቆዋል።!!!!!!








All the contents on this site are copyrighted ©.