2010-04-07 18:37:18

ክርስቶስ ከሞት እንደተነሣ የሚያውቅ ክርስትያን ለመመስከሩ ደፋር ነው።


የክርስቶስ ትንሣኤ ታሪካዊ ሐቅና መልዕልተ ባህርያዊ ነው፣ ለዚሁ ምስጋና ይድረሰውና ክርስቶስ ከሞት በፊት ወደ ነበረው ሁኔታ አይመለስም በሞት አድርጎ ወደ አዲስ የሕይወት አድማስ ይሸጋገራል። ቅዱስ አባታችን ሥልጣን ከያዙ ወዲህ በተለያዩ ግዝያት ለምእመናን የፋሲካን ምሥጢር አስተምረዋል። ምሥጢሩን ሲገልጹ “ክርስቶስ በዚህ ምሥጢር በመጀመርያ ምስክሮቹን ከማርያም መግደላዊት እስከ ሐዋርያት ጠርተዋል ከዛም ለሁለት ሺህ ዓመታት እያንዳንዱ ክርስትና የገባን ይህንን ምሥጢር በግልጽ ለዓለም ሙሉ እንዲሰብክ እየጠራ ነው” ብለዋል።

አምና ባስተማሩት ትምህርት፣ በጎልጎልታ በመስቀል ተንጠልጥሎ ሞት የጥንቱ ፋሲካ ጨካንና ሐዘን የበዛበት ዋዜማ ቢሆንም ቅሉ እያንዳንዱን በደስታ የሚውጥ ተከታይ የበዓል ዕለት ነው፣ የታሪክ ሂደትን የለውጠ ትልቁ የትንሣኤ ሥራ ከህዝብ ዓይንና ከውካታው ተሰውሮ ተከናወነ፣ ይህንን ፍጻሜ በፍጥረታቸው የተወሰኑ ሕዋሶቻችን እንዲቀበሉት ተነግሮም ቢኖር ክርስቶስ ዜናውን ለመዘርጋት በመጀመርያ መቃብሩን ዘግቶ የነበረ ትልቁን ድንጋይ በመክፈት ተጨባጭ ምስክርነት ይሰጣል፣ ለትንሣኤው ከሚቀርቡ ማስረጃዎች አንዱ እርሱ ራሱ ነው፣ ከሞት ከተነሣ በኋላ ለሚያውቁትና ሲሞት ላዩት በሕይወት ታያቸው። “አንቺ ሴት ለምን ታለቅሻለሽ፣ ማንን ትፈልግያለሽ” ይህ በዕለተ ትንሣኤ የሚነበብ ቃለ እግዚአብሔር ነው፣ ይህ ጥያቄ የቀረበላት በሞቱ እጅግ ኣዝና ለነበረች ለማርያም መግደላዊት ነው፣ ሕያው መሆኑን አሳየ ሲል ኢየሱስ እንደገና እንደ አልአዛር ወደ ነበረበት ሕይወት ተመለሰ ማለት አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ቅዱስ በርናርዶስ “እኛ የምናከብረው ፋሲካ መሸጋገርን እንጂ ወደ ነበረበት መመለስን አያመለክትም፣ ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ሌላ ሕይወት ተሸጋገረ እንጂ ቀድሞ ወደ ነበረው ሕይወት አልተመለሰም” ይላል።








All the contents on this site are copyrighted ©.