2010-04-06 16:12:39

“ለአምላክ እንዘምር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና” (መጽሐፈ ሰዓታት ዘትንሣኤ አንደኛ ምልጣን)


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ

የትንሣኤን አዋጅ ብእነዚሁ የሥርዓተ አምልኮ ቃላት አቀርብላችኋለሁ፣ ይህ ዜማ እስራኤላዉያን ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ በኋላ የዘመሩት ጥንታዊ የምስጋና መዝሙር ነው። ኦሪት ዘፀኣት (ምዕ:15:19-21) እስራኤላውያን ባሕርን በደረቅ ምድር ከተሻገሩ በኋላ፣ ግብጻውያን በውኃ ውስጥ መስጠማቸውን ባየች ጊዜ የሙሴና የአሮን እኅት ሚርያም እና ሌሎች ሴቶች ይህንን የደስታ መዝሙር በመዘመር ጨፈሩ። “አስደናቂ በሆነ መንገድ ድል ለተቀዳጀ ለአምላክ ዘምሩ፣ ፈርሱና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሎአል፣”።

በመላው ዓለም ያሉ ክርስትያን ደግሞ በትንሣኤ ዋዜማ ይህንን እንደገና ይዘምራሉ፣ በትንሣኤ ሙሉ ብርሃን የምናስርገውና በደስታ የምናደርገው ልዩ ጸሎትም የዚህ መዝመኡር ትርጉም ይገልጻል። ጸሎቱም እንዲህ ነው፣ “አባታችን ሆይ ከዘመናት በፊት ያደርግኃቸው ተአምሮች አሁንም አስደራንቂነታቸውን እናያለን፣ አንዴ አንድ ሃገርን ብቻ ከባርነት አዳንክ፣ ዛሬ ግን ያንን ድኅነት በጥምቀት ለሁሉም ትሰጣለህ፣ የዓለም ሕዝቦች በሙሉ የአብርሃም ልጆች በመሆን የእስራኤል ወራሾች ለመሆን ብቃት እንዲኖራቸው ዘንድ እንለምንሃለን”።

ወንጌል የጥንቱ አምሳሎች እንደተፈጸሙ ገልጾልናል፣ በሞቱና በትንሣኤው ኢይሱስ ክርስቶስ ከመሠረታዊ የኃጢኣት ባርነት ነጻ አወጣን፣ በምድረ ተስፋ ለሚመሰለው የእግዚአብሔር መንግሥት ዓለም አቀፍ የፍትህ የፍቅርና ይሰላም መንግሥት ጐዳናን ከፍቶልናል።

ይህ የነጻነት ጉዞ (ዘፀአት) መጀመርያ በሰው ልጅ ውስጥ ይከናወናል፣ ይህም ኢይሱስ በምሥጢረ ፋሲካ ይሰጠን የምሥጢረ ጥምቀት ሳቢያ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ እንደግነኣ በመወለድ ይከናወናል። አሮጌው ሰው ቦታውን ይለቃል፣ አሮጌው ሕይወት ኋላ ቀርቶ አዲስ ሕይወት መጀመር ይቻላል። ይህ የነጻነት ጉዞ ግን የEጠቃላይ ነጻ መውጣት መጀመርያ ነው፣ በሁሉም መስክ ማለት በሰብአዊ ግላዊና ማኅበራዊ አመለካከት ነጻ የሚያወጣን ነው።

እርግጥ ነው ወንድሞቼና እኅቶቼ ፋሲካ እውነተኝ የሰው ልጆች መዳን ነው። የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስ ደሙን ስለእኛ ያፈሰሰው ባይሆን ኖሮ ምንም ተስፋ የሌላቸው በሆንን ነበር፣ የእኛና የመላው ዓለም ዕጣ ፈንታም በእርግጥ ሞት በሆነ ነበር። ፋሲካ ግን ይህንን ሂደት ተቃራኒ ትርጉም እንዲኖረው አደረገው፣ የክርስቶስ ትንሣኤ አዲስ ፍጥረት ነው፣ ለማዳቀል ተቆርጦ እንደሚተከለው ቅርንጫፍ አዲሱን ተክል አዲስ ሕይወት በመስጠት ተክሉን በሙላት እንደሚያፈልቅ ሁሉን አሳደሰ። ለአንዴና ለሁላችን የመልካም የሕይወትና የምሕረት ጐንን እያዳላ የታሪክን ሂደት ከመሠረቱ የለወጠ ፍጻሜ ነው።

ነጻ ነን፣ ድነናልም፣ ስለዚህ ከልባችን የመነጨ “ለአምላክ እንዘምር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና” በማለት እናስተጋባ። ከጥምቀት ውኃ የወጣው ክርስትያን ሕዝብ ሁሉ በአዲስ ሕይወት ከኃጢኣት ነጻ የውጣና ጥንተ መልካምነቱ የሆኑ እውነት በጎነት በተመላልሰ ባህርይ የቆመውን የፍሲካ ፍሬ ለሁሉም ሕዝብ ለማዳረስ የዚህ ድኅነት ምስክር ለመሆን የተላከ ነው። ባለፉት ሁለት ሺሕ ዓመታት ክርስትያን በተለይም ቅዱሳን በሕይወታቸው በኖሩትና በመሰከሩት ምሥቲረ ትንሣኤ ታሪክን ፍርያማ አድርገውታል።

ሁል ጊዜ ምሥጢረ ፋሲካን ስለምታዘወትርና በሁሉም ጊዜና ቦታም አሳዳሽ ኃይሉን ስለምትሰብክ ቤተ ክርስትያን በነጻነት ጉዞ ያለ ሕዝብ ናት። በዘመናችን የሰው ልጆች የንጻነት ጉዞ ያስፈልጋቸዋል አፍአዊ ማስተካከል ሳይሆን መንፈሳኢና ሞራላዊ ለውጥ ያስፈልጋል። ከእያንዳንዳችን ኅሊና ጀምሮ ሥር ነቀል ለውጥ ከሚያስፈልገስ ጥልቅ ቀውስ ነጻ ለሙጣት የወንጌል ድኅነት ያስፈገዋል።

በመሀከለኛው ምሥራቅ በተለይም በጌታ ሞትና ትንሣኤ በተቀደሰው መሬት ውስጥ ያለው ሕዝብ ከውግያና ከዓመጽ ወደ ሰላምና ስምምነት እውነተኛ ወሳኝ የነጻነት ጉዞ እንዲያደርጉ ጌታ ኢየሱስን እለምናለሁ።

በፈተናና በሥቃይ የሚገኙ ማኅበረ ክርስትያን በተለይ የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያኖች ክሞት የተነሣው ጌታ ለሓዋርያት ብላየኛ ክፍል የተናገረውን አጽናኝና አበራታች ቃላት ዛሬም ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን እንዲላቸው ዘንድ እመኛለሁ።

ዕፀ ፋርስን ከማስተላለፍ ጋር የተያይዙ አደገኛ ወንጀሎች እየተነሡ የሚታይባቸው የላቲን አመሪካና የካሪብያን አገሮች የጌታ ትንሣኤ ሰላም አብሮ መኖርና ይጋራ ጥቅምን ማክበር አሸንፊነት ምልክት ይሁንላቸ ዘንድ እመኛለሁ።

በኃይለኛውየምድር መንቀጥቀጥ የተጐዳሁ ውድ የኃይቲ ሕዝብ ከኃዘንና ተስፋ መቍረጥ ወደ በዓለም አቀፍ አጋርነት የተደገፈ አዲስ ተስፋ የነጻ መውጣት ጉኦ ያድርጉ ዘንድ እመኛለሁ።

ሌላ ትልቅ የመሬት መናወጥ ጥፋት ይሳለፉ ወ የቺለ ሕዝብ ብእምነታቸው ተደግፈው በጽናት ደግሞ የማነጽ ግዳጃቸውን እንዲወጡ እመኛለሁ።

ከሙታን ተለይቶ በተነሣው ኢይሱስ ኃይል በአፍሪቃ ውስጥ ያለማቋረጥ ጥፋና ስቃይ እያስከተሉ ያሉ ግጭቶች አብቀትወ የሥልጣኔ ዋስትና የሆኑ ሰላምና ዕርቅ እንዲነግሡ እመኛለሁ።

በተለይም የደሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ጊኒ እና ናያጀርያን ዕጣ ፈንታለጌታ አማጥናለሁ።

እንደ በትፓኪስታን የአሰሉ አግሮች ስለእምነታቸው ስደት ሞትም ሳይቀር የሚቀበሉ ክርስትያን ከሙታን ተለይት የተነሣው ክርስቶስ ይደፋቸው ዘንድ ምኞቴን እገልጻለሁ።

በሽብር በማኅበረ ሰባዊና ሃይማኖታዊ መለያየቶች የሚሰቃዩትን አገሮች ጌታ የውይይትና አብሮ በሰላም የመኖር ጸጋ እንዲሰጣቸው እለምናለሁ።

የምጣኔ ሃብት የገንዘብ እንቅስቃሴ በእውነት በፍትሕና በወንድማማዊ መረዳዳት እዲቀይሱ ይህ ትንሣኤ ለዓለም መሪዎች ብርሃንና ኃይልእንዲሰጣቸው እመኛለሁ።

የእያንዳንዱን ሰው ሕይወት ክብር የሚጥበቅበትና ሁሉም የሚቀበልበት በፍቅርና በእውነት የተመሠረተ መጪ ትውልድ ለመገንባት አዳኝ ኃይል ያለው የክርስቶስ የትንሣኤ ኃይል ያለነው የሞት ባህል የሚያስከትለውን ችግር ለማሸነፍ ያስችለን ዘንድ እመኛለሁ።

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ ፋሲካ በአስማት ኃይል አደለም የሚሠራው። ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ በኋላ ዕብራውያን ምድረ በዳን ነው ያገኙት፣ እንዲሁም ቤተ ክስትያን ከትንሣኤ በኋላ ታሪክን ዘወትር ከደስታዎቹና ከተስፋዎቹ እንዲሁም ከሥቃዮቹና ከጭንቀቶቹ ጋር ነው የምትጋፈጠው። በአጠቃላይ ይህ ታሪክ ተለውጠዋል፣ በአዲስና ዘለዓለማዊ ኪዳን ተመልክታለች ለሚመጣው ትውልድም ክፍት ናት። ስለዚህ በተስፋ ድነን “ለአምላክ እንዘምር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና” የሚለውን ዘወትር አዲስ የሆነውን ጥንታዊ መዝሙር በልባችን እየዘመርን ንግደታችንን እንቀጥል። ብለው የፋሲካ መልእክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች የመልካም ፋሲካ ምኞታቸውን ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.