2010-04-04 12:05:30

ቤተ ክርስትያን ቅሌትን አወገዘች፡


ከአሁን በፊት ቤተ ክርስትያን የፍትወተ ስጋ ዓመጽ በሕጻናት ላይ እንዳይፈጸም አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ተዘጋጅታለች ይህንን መግለጫ የሰጡ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ናቸው ።

ቃል አቀባዩ ይህንኑ መግለጫ የሰጡበት ምክንያት በአንዳንድ የኤውሮጳ ሀገራት ከአሁን ቀደም በየቤተክርስትያን አባላት በሕጻናት ላየ የተፈጸሙ በሕጽናት ላይ የተፈጸሙ የፍወተ ስጋ ዓመጾች ተነስተው አነጋጋሪ ሆነው በመሰንበታቸው ምክንያት እንደሆነ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

በረፓብሊክ አይርላንድ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በተፈጠረው አሳሳቢ ጉዳይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ከየሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ተወካዮች እና ከጠቅላላ ጳጳሳቱ ጋር መነጋገራቸው ለቤተክርስትያኒቱም ይህ አስከፊ ጉዳይ በተመለከተ አንድ ሐዋርያዊ መልእክት ለማስተላለፍ እየተዘጋጁ መሆናቸው ቃል አቀባዩ አመልክተዋል።

ከረፓብሊክ አይርላንድ ሌላ በጀርመን አውስትርያ እና ኔዘርላንድስ በተመሳሳይ እኤአ በሃምሳዎቹ በቤተክህነት አባላት በሕጻናት ላይ የተፈጸሙ የፍትወተ ስጋ ዓመጽ መገለጽ መጀመራቸው የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ጠቅሰው ፡ የሀገራቱ ረኪበ ጳጳሳት በዚያን ግዜ የተበደሉ ሕጻናት አደባባይ ወጥተው ያጋጠማቸው ችግር እንዲገልጡ እና የተባከውን አስከፊ ተግባር የተፈጸሙ እንዲጋለጡ ማድረጋቸው አስገንዝበዋል።

አስጸያፊ የሆኑ ተግባሮች እንዲገቱ እና ይንኑ የሚፈጽሙ የቤተክርስትያን አባላት ይሁኑ አይሁኑ ድርጊታቸው በማውገዝ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ እና በፈጸሙት አሳፋሪ ድርጊት እንዲቀጡም የቤተክርስትያን ፍላጎት መሆኑም አያይዘው መግለጻቸው ተመልክተዋል።

የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ እንደገለጡት የአውትርያ ጉዳይ ሲታይ በየቤተ ክህነት አባላት ዓመጽ የተፈጸመባቸው አስራ ሰባት ሕጻናት ሲሆኑ ሀገሪቱ ውስጥ ከቤተክርስትያን ውጭ የፍትወተ ስጋ ዓመጽ የተፈጸመባቸው ሕጻናት አምስት መቲ አስር መሆናቸው የሀገሪቱ አጣሪ ኮሚሽን ማረጋገጹ ገልጠዋል።

በአጠቃይ አስከፊ እና አሳፋሪ ተግባሩ ፍጹም መገታት እና መወገዝ ያለበት ሐጢአት ከመሆኑ ባሻገር ትልቅ ወንጀል መሆኑ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አመልከተዋል።

በመሆኑም የጀርመን የቤተ ሰብ ሚኒስቴር በሕጻናት ላይ የተፈጸመው የፍወተ ስጋ ዓመጽ ጠንቅ ለመዳሰስ እና ለመፈወስ ቤየክርስትያን ያሳተፈ የውይይት መድረኽ እንዲከፈት ያቀረበው ሐሳብ ሸጋ መሆኑ ቃል አቀባዩ ጠቅሰው የጀርመን መንግስት ቻንስለር ኤንገላ መርክል የሀገሪቱ ቤተክርስትያን በተከሰተው አስከፊ ድርጊት ላይ የወሰድችውን አቋም ማመስገናቸው አስታወቅዋል።

ቤተክርስትያን ከሕብረተ ሰብ ጋር አብራ ስለምትኖር በሕብረስተሰቡ ላይ የፈጸመ ይፈጽማቸው አስከፊ ድርጊቶች ሁሉ ታወግዛለች ሐለፊነትዋም ትሸከማለች ያሉት የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በዚሁ አስቃቂ ሁኔታ እየተሰቃየች የምትገኘው ቅድስት ሮማዊት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ከዚሁ ክስተት በመገላገል ንጽህናዋ ጠብቃ መኖር ትችላለች በማለት ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.