2010-03-26 16:25:26

የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ


ባለፈው ሳምንት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ወደ አየርላንድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በጻፉት መልእክት የብዙኃን መገናኛ የተለያየ ትርጓሜ በመስጠት እየተቹ ናቸው።

ከእነዚህ ጋዜጣዎች አንዱ ኒው ዮርክ ታይምስ ከ20 ዓመታት በፊት ስለነበረው የአባ ለውረንስ መርፍይ ጉዳይ አንስቶ ላቀረበው ሂስ የቅድስት መንበር የጋዜጣና የኅትመት ኃላፊ ቃል አቀባይና የረድዮ ቫቲካን ዋና አስተዳደሪ፣ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚከተለውን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። “የሚልዋኪ ሃገረ ስብከት አባል የነበሩ የአባ ለውረንስ መርፊ አሳዛኝ ጉዳይ በተለይ የሚከላከል የሌላቸው ተጐጂ ወገኖችን ማሰቃየቱ ነው። በሕጻናት ላይ ተገቢ ያልሆነ ጾታዊ አድራጎት በመፈጸሙ አባ ለውረንስ መርፊ ሕግን ጥሰዋል፣ የባሰው ደግሞ በእርሱ ላይ የተጣለውን መንፈሳዊ ኃላፊነት አዋርደዋል። ብስልሳዎች አጋማሽ ላይ የአባ መርፊ ሰለባ የሆኑ ክስ አቅርበው ነበር፣ የሲቪል ባለሥልጣናትም አስፈላጊውን እርምጃ ወስደው ነበር።

መንገበ ሃይማኖትን የምትጠብቅ ማኅበር ጉዳዩ ከተፈጸመ ከሃያ ዓመታት በኋላ ነው መረጃ የደረሳት።

እ.አ.አ በ1962 ዓ.ም. ቤተ ክርስትያን በምሥጢረ ኑዛዜ ሰበብ የጾታዊ ዝንባሌ አነሳሽነት ወይም ምክንያት እንዳይኖርና የክህነት ጥሪአቸውን በመዘንጋት በተለያዩ የእርኩስ ዝሙት ተግባር ለተገኙ የቤተ ክህነት አባላትን ለመመርመርና ተገቢ ቅጣት ለመስጠት ክሪመን ሶሊቺታስዮኒስ ማለት የማባባል ወንጄል በሚል ርእስ በሕገ ቆነና የተመሠረተ አመራርና ሕግ አውጃ ነበር፣ ይህም እ.አ.አ. ብ2001 ዓ.ም. በአዲሱ ሕገ ቆነና መሠረት ተሻሽሎ ደ ደሊክቲስ ግራብዮሪቡስ “አደገኛ ስለሆኑ ውንጄሎች” በሚል ርእስ ተሻሽሎ ወጣ።

በኒው ዮርክ ታይምስ በወጣው ዘገባ በአባ መርፊ ጉዳይና በክሪመን ሶሊቺታስዮኒስ ግኑኝነት ነበር የሚለው ከእውነት የራቀ ነው፣ ምንም ዓይነት ግኑኝነት የላቸውም። ጋዜጣው እንደሚያመልከተው ሳይሆን በክሪመን ሶሊቺታስዮኒስም ይሁን በሕገ ቆኖና በሕጻናት ላይ ተገቢ ያልሆነ ጾታዊ ዓመጽ ላደረሱት ለሕግ አስከባሪዎች እንዳይከሰሱ የሚከልክል የለም።

ጉዳዩ በሰበካው ባለሥጣናትና በፖሊስ ክስ ተመሥረቶበት ከታየ ከሃያ ዓመታት በኋላ በዘጠናዎች መጨረሻ ላይ የእምነት ጉዳይን የምትከታተል ማኅበር ለመጀመርያን ጊዜ የአባ መርፊን ጉዳይ በሕገ ቆኖና እንዴት እንፍረደው የሚል ጥያቄ ከሃገረ ስብከቱ ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ይህ ጥያቄ የቀረበው በክሪመን ሶሊቺታስዮኒስ እንደተመለከተው በኑዛዜ ላይ የተፈጸመ የማባባል ወንጀል ሆኖ እንጂ በሲቪል ባለሥልጣኖች እንደሚፈረድና ተገቢውን ቅጣት እንደሚጠይቅ ዓይነት አልነበረም።
ሕገ ቆኖና ቍ.1395 ክፍል 2 የዚህ ዓይነት ጉዳይ በሚያጋጥምበት ጊዜ ወዲያውኑ የቅጣት እርምጃ እንዲወሰድ አይጠይቅም ግን እስከ ከክህነት መዓርግ ወደ ምእመን ደረጃ የማውረድ ቅጣትን ያዝዛል። ይህ በእንዲህ እያለ ኣባ መርፊ ያኔ በሕመም ያልጋ ቍራኛ ሆነው ለሞት የሚጠባበቁ በመኖራቸው ላለፉት ሃያ ዓመታት ደግሞ ተነጥለው ለብቻቸው ከመኖር በላይ ምንም ዓይነት ክስ ስላልተመሠረተባቸው የእምነት ጉዳይን የምትከታተል ማኅበር ለሚልዋኪ ሊቀ ጳጳስ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባ መርፊ ምንም ዓይነት ሕዝባዊ ኃላፊነት እንዳይሰጣቸው እንዲሁም ላደርጉት ጥፋት ሙሉ ኃላፊነት እንዲሸክሙ ይሁን ብላ መልስ ሰጥታ ነበር፣ አባ መርፊ ምንም ጥፋት ሳይፈጽሙ ከአራት ወራት በኋላ አርፈዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.