2010-03-23 18:31:40

የክህነት ዓመት፣ የምስክርነት ዓምድ


በኢጣሊያ ቸሰና ከተማ የሚገኘው ካቴድራል ቆሞስ ኣባ ጆርዳኖ አማቲ ዘንድሮ በመከበር ላይ ስላለው የክህነት ዓመት ምክንያት ከቫቲካን ርዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ስለ ክህነት ጥሪአቸው ሲመሰክሩ፣ የዛሬ 30 ዓመት በፊት በቤት ክርስትያን ፈቃድ መሠረት የክህነት ማዕርግ እንደተቀበሉ በማስታወስ፣ በማርቶራኖ ከተማ ቤታኒያ በሚል መጠሪያ በተለያዩ ችግር ምክንያት ለክብር ሰራዥ አደጋ ተጋልጠው የሚገኙት ስደተኞች ሴቶች በመቀበል በማስተናገድ መንፈሳዊ ስብአዊ ማኅበራዊ ሕንጸት በመለገስ ኑሮአቸው እንዲያሻሽሉ መብታቸውን እና ግዴታቸውንም በማወቅ እራሳቸውን በማስከበር እንዲኖሩ የሚያደርግ በክልሉ ከሚገኘው በካሪታስ የሚጠራው የካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ቅርጫፍ ጋር በመተባበር የሚሠራ የግብረ ሰናይ ማኅበር ያቋቋሙ መሆናቸውም በመግለጥ፣ በስደተኛው ላይ በተደጋጋሚ የሚሰጠው አሉታዊ ቅድመ ፍርድ፣ ምክንያት የሚፈጠረው የልዩነት አጥር እንዲወገድ የሚጥር የግብረ ሰናይ ማኅበር መሆኑ አስረድተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.