2010-03-23 18:30:01

የቲዮሎጊያ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ፣ የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለአየርላንድ ቤተ ክርስትያን ያስተላለፉት መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአየርላንድ በውልደ ክህነት አባላት ስለ ተፈጸመው የአወሲብ አመጽ ርእሰ ማእከል ያደረገ፣ ለአየርላንድ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ ለውሉደ ክህነት እና ለዓለማውያን ምእመናን ሓዋርያዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

የአየርላንድ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የአርማግ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ ካርዲናል ሲን ብራድይ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሓዋርያዊ መልእክት የአየርላንድ ቤተ ክርስትያን ተሃድሶ የሚያነቃቃ ነው በማለት አስተያየት ሰጠዋል።

በኢጣልያ የኪየቲ ቫስቶ ሊቀ ጳጳስ የቲዮሎግያ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ፣ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቅዱስ አባታችን አባታዊ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት እና ሰብአዊነትን የምታጎላ ሓዋርያዊ መልእክት የአኗኗር ስልት፣ ይኽ ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ እውነት ብሎ የሚገለጠው ሓሳብ መሆኑ በማስረዳት፣ እውነት ለመኖር እና ለመናገር እግዚአብሔረ ሓቅ መሆኑ ማእከል ያደረገ የአኗኗር ስልት መከተል አስፈላጊ እና ግዴታ መሆኑ፣ የምታሳስብ ነች ካሉ በኋላ መልእክቱ ለበደለው ለተበደለው በሌላው ረገድ ለቤተሰብ ለወጣቱን ክፍለ ኅብረተሰብ እንዲሁም ለውሉደ ክህነት በጠቅላላ ለአየር ላንድ ማኅበረ ክርስትያን የተላለፈች ነው ብለዋል።

ወንጌላዊ ሕይወት ምን ማለት መሆኑ የምታስረዳ፣ እግዚአብሔር ደስ ለማሰኘት በእርሱ ለመታመን የምታነቃቃ፣ በጊዝያዊ ደስታ የተለካ ሕይወት ከመኖር መቆጠበ የላቀ እና በእስይታ የተካነ ሕይወት መኖር ምን ማለት መሆኑ የምታስረዳ ነች ብለዋል። ወንጀል የፈጸመውን በሰው እና በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂነቱን የምታጎላ በፈጸመው ተግባር እንደሚፈረድበት በመተንተን፣ ነገር ግን የእግዚአሔር ምህረት ወሰን የሌለው መሆኑ የምታስገንዘብ፣ የእግዚአብሔር ምህረት የይገባኝ ጥይቄ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑና ቤተ ክርስትያን የወሲብ አመጽ የተፈጸመባቸውን ከደረሰባቸው ሰብአዊ መንፈሳዊ እና ስነ አእምሮአዊ ተጽእኖ ለማላቀቅ በሚደረገው ጥረት ተቀዳሚው ሚና ከመጫወት ወደ ኋላ እንደማትል የሚያረጋገጥ ሓዋርያዊ መልእክት ነው በለዋል።

ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወዲህ በቤተ ክርስትያን የታየው የጥሪ ግሽበት በሚገኘው ጥቂት ጥሪ ላይ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረው ጥልቅ ክትትል እና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት ላላ እንዲል አድርጎታል፣ በዘርአ ክህነት ተማሪዎች ላይ የሚደረገው ክርስትያናዊ ሰብአዊ ማኅበራዊ ስነ አእምሮአዊ ሕንጸት እና ክትትል ላላ በማለቱ ምክንያት፣ አንዳንድ ስሜታዊ ጾታ የመቆጣጠር ብስለት የሌላቸው ወይንም መረጋጋት የሌላቸው፣ ማእረገ ክህነት እስከ መቀበል አድርሰዋል። የጥሪ ግሽበት ለመሸፈን ዘረአ ክህነት ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ለማግበስበስ እና የዘርአ ክህነት ተማሪው ሁሉ የክህነት ማእርግ እንዲቀበል ምክንያት ሊሆን አይችልም። ጥሪ ይነስም ይብዛም የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት ዘወትር በሳል መሆን አለበት። ስለዚህ የቅዱ አባታችን ሐዋርያዊት መልእክት ይኸንን ሁሉ ለየት ባለ አነጋገር የምትገልጥ ነች ካሉ በኋላ፣ በመጨረሻ ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር መሆን ምን ማለት መሆኑ የምታስረዳ፣ ቤተ ክርስትያን ሥጋ ለብሶ የወረደው የግዚአብሔር ቤት ክርስትያን ነች፣ ሰብአዊው እና መለኮታዊ ባህርይ ሳይከፋፋል ነገር ግን ሳይደባለቅ ሳይለያይ የሚገለጥባት ነች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.