2010-03-22 18:00:38

የአቡነ ቡሩክ በዓል በሞንተካዚኖ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ትናንትና በሞንተካሲኖ በሚገኘው የአቡነ ቡሩክ ገዳም መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል። አቡነ ብሩክ የኤውሮጳ ጠባቂም ነው፣ ብፁዕነታቸው በመሥዋዕተ ቅዳሴው ባሰሙት ስብከት “ቅዱስ በነደቶ እንደ ምልክት የተጠቀመባቸው ማረሻና መስቀል ናቸው፣ ለኤውሮጳ አንድነት ቋሚ ምልክት የሆኑት በትሕትናቸው አለማወቃቸውን በማወቃቸውና አውቀውም እንደደንቆሮ በመኖር ባሳዩት የክርስቶስ ሕይወት ዛሬም ኤውሮጳ በባህልዋና በሥልጣኔዋ ያለውን የክርስትና መሠረት መክዳት የለባትም” ሲሉ አቡነ ቡሩክ የሰላም አብነትና በሕዝብ መካከል የዕርቅ ምሳሌ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ብፁዕነታቸው ቅዳሴ ከመግባታቸው በፊት የፍትሕ የሰላምና የወንድማምችነት ጠባቂ የሆነ የአቡነ ቡሩክ ሕግ ለኤውሮጳ ብቻ ሳይሆን በሁከት ላሉት የመሀከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለአፍሪቃና ለሁሉም የሚሆን የሰላምና የብልጽግና መሣርያ መሆኑንም ገልጠው ነበር። በቅዳሴው የገዳሙ አባላት በሙሉ እና የቦታዊ የፖሎቲካና አስተዳደር ባለሥጣናትም ተካፍለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.