2010-03-19 17:39:15

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም


በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ግጽው ትናንትና የቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌምን አስታወሰች፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም በአራተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ የቤተ ክርስትያን ሊቅ ናቸው።

ቅዱስ አባታችን ሰኔ 27 ቀን 2007 ዓም ብቀረቡት የዕለተ ሮቡዕ ሳምንታዊ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ስለዚሁ ቅዱስ አስተምረው ነበር። ያኔ በስጡት ትምህርት “ቅዱስ ቄርሎስ ትሑትና ጽኑ ሰው ነበሩ፣ ያኔ ከነበሩ የመንግሥት ባለሥልጣናት ብዙ ግፍ ደረሰባቸው፣ ቤተ ክርስትያንም ከዛ ባላነሰ እንዲሰቃዩ አደረገች። በ348 የኢየሩሳሌም ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል፣ የኢየሱስን አምላክነት ከካዱ ኣርዮሳውያን ጋር በመከራከራቸው ሦስት ጊዜ ለስደት ተዳረጉ። ከቤተ ክርስትያን አባሎችም ሳቅይቀር ብዙ ከተሰቃዩ በኋላ አምስት ዓመት ከመሞታቸው በፊት ወደ መንበራቸው ተመለሱ፣ ከ15 ዘመናት በኋላም በ1882 በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልዮን 13ኛ የቤተ ክርስትያን ሊቅ ተባሉ፣ በቤተ ክርስትያን መባቻ ምሥጢራተ ያስተማሩት ትምህርትና ስብከቶቻቸው ወደር የሌላቸው የመንፈሳዊ ዕውቀት ምንጮች በመሆን ለቤተ ክርስትያን እስካሁን ያገለግላሉ። የቅዱስ ቄርሎስ ስብከቶች በዘዴ የተዘጋጀ ትምህርተ ክርስቶስ ናቸው፣ በምልክቶች ሃብታም የሆኑ ትምህርቶች በማቅረብ እውነተኛ የሰው ልጅ ነጻነት በእግዚአብሔር መጠጋትና ከቤተ ክርስትያን ጋር አንድ መሆን ነው” ብለው ያስተምሩ ነበር።

የትምህርተ ክርስቶስ ተማሪዎችን “ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት “የሰው አጥማጆች ትሆናላችሁ” ያለውን በማስታወስ “አንተም በቤተ ክርስትያን ወጥመድ ተጠምደሃል፣ በወጥመዱ ከተጠመድክ ወጥመዱ በሕይወትህ እንዲያጠምድህ ለመሸሽ አትሞክት፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ሞትን ሳይሆን ከሞት በኋላ ህይወት እንዲሰጥህ ከእርሱ ጋር አንድ ያደርጋሃል፣ ጳውሎስ ወደ ሮማውያን ምዕ 6 ቍ 11 ላይ እንደጻፈው ሕይወት ለማግኘት መሞት አለብህ፣ ለኃጢአት ሙት ከዛሬ ዕለት ወዲህ በጽድቅ እንድትኖር ይሁን፣” ይላቸው ነበር።
ስለ ምሥጢረ ጥምቀትም ሲናገር “ከጥምቀት በፊት በጨለማ ስትመላለሱ ምንም ማየት አትችሉም ነበር ከጥምቀት በኋላ ግን በቀን ብርሃን ስለተገናችሁ ሁሉን ማየት ትችላልችሁ ይላል፣ ስለዚህ እግዚአብሔር ክርስትናን እንድንማርና የፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው የሆነ ኢየኡስ ምስክሮች እንድንሆን ያብቃን ዘንድ እንጸልይ” ብለው እንደነበር የሚታወስ ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.