2010-03-19 17:35:54

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለአየርላድ ካቶሊካውያን የጻፉት ሐዋርያዊ መልእክት ነገ ቅዳሜ ይፋ ይሆናል።


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ሮብ በሳምንታዊ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ እንደገለጹት፣ ዛሬ ዕለት በቅድስት ቤተ ሰብ ጠባቂና የዓለም አቀፍ ቤተ ክርትያን ጠበቃ በሆነው ቅዱስ ዮሴፍ በዓል፣ በአንዳንድ የአየርላድ ካቶሊካውያን ቤተ ክህነት በሕጻናት ላይ በተፈጸሙት ተገቢ ያልሆነ አድራጎት እጅጉን ለተናወጠችው የአየርላድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በጻፉት መልእክት ፊርማቸውን እንዳኖሩና መልእክቱም ነገ ቅዳሜ ይፋ እንደሚሆን ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል።

በአጠቃላይ የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ ባስተማሩት ወቅት ቅዱስነታቸው “ይህ መልእክት፦ በሚጸመው የንስሐ፣ የመዳንና፣ የመታደስ ሂደት ይረዳል የሚል ተስፋ አለኝ። ሁላችሁ በክፍት ልብና በእምነት መንፈስ እንድታነቡት አደራ እላለሁ።” ብለው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ነገ ቅዳሜ በሮም አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የቅድስት መንበር የዜናና የኅትመት ክፍል ኃላፊ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ መልእክቱን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጣ ዜና ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.