2010-03-17 18:47:23

የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ለኢጣልያ ኢንዳስትሪ ባለሃብቶች ማኅበር “የግል ንግድ ድርጅቶች ሰብአዊ ዕሴቶን የሚጠብቅና የኅብረተሰቡን የጋራ በጎ የሚያተኵር እንዲሁም በሁሉም የሚደገፍ ብልጽግና የሚያራምዱ መሆን እንዳለባቸው” አመልክተዋል።

ብፁዕነታቸው ይህን ያሉት ትናንትና በተካሄደው የኢጣልያ ኢንዱስትሪ ባለሃብት ድርጅቶች ስብሰባ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው። ብፁዕነታቸው ቅዱስ ኣባታችን በካሪታስ ኢን ቨሪታተ ሐዋርያዊት መልእክት ያሰፈሩትን በማስታወስ አዲስ እውነተኛና የሚደጋገፍ ብልጽግና ለመፍጠር በፖሎቲካ በምጣኔ ሃብትና በንግድ ዘርፍ ማበርከት የሚችሉ አዲስ የክርስትያን ትውልድ እንዲኖሩ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስትያንን ከመጠን በላይ የሚያሳዝንዋትና እንድታርማቸው ኃይለኛ እርምጃ የምትወስድባቸው በሕጻናት ላይ በተፈጸሙት ተገቢ ያልሆነ አድራጎቶችን በማመልከት “ቤተ ክርስትያን በምእመናን ገና ትልቅ ታማኝነት አላት ሆኖም ግን ይህንን መታማመን ለማደፍረስ የሚጥር አይጠፋም፣ ቤተ ክርስትያን ግን ሁል ጊዜ ከላይ የሚመጣ ልዩ እርዳታ አላት” ብለዋል።

ባለነው የሥልጣኔ ዘመን እንደ ወረርሽኝ የያዘው ምን ያህል ያወጣል የሚለው አስተሳሰብ ሳይሆን ምን ጥቅም አለው፣ ዕሴቱስ ምንድር ነው ማለት ያስፈልጋል፣ ይህ ነው ለፋብሪካ ውጤቶች ክርስትያናዊ ትርጉም ሊሰጥ የሚችል፣ ትርፍን ብቻ በማሰብ የሚደረግ ድርጅታዊ እንቅስቃሴ ለሰብአዊና ክርስትያናዊ ዕሴቶች ቅድሚያ ሊሰጥ አይችልም፣ ስለዚህ “የግል ንግድ ድርጅቶች ሰብአዊ ዕሴቶን የሚጠብቅና የኅብረተሰቡን የጋራ በጎ የሚያተኵር እንዲሁም በሁሉም የሚደገፍ ብልጽግና የሚያራምዱ መሆን አለባቸው” ሲሉ በጉባኤው ለተገኙት ቤተ ክርስትያን ስለ የንግድ ድርጅቶች ያላትን አስተያየት በሰፊው ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.