2010-03-12 13:55:41

የደቡብ ሱዳን ተፈናቃዮች



 


እ.ኤ.አ. በደቡብ ሱዳን የነበረው የርስ በርስ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተደረገው ጥረት ባረጋገጠው የሰላም ስምምነት፣ በጦርነቱ ሳቢያ ቤትን እና ንብረቱን ጥሎ ለመፈናቀል አደጋ ተጋልጦ የነበረው ሁለት ሚሊዮን RealAudioMP3 የሚገመት የክልሉ ነዋሪው ሕዝብ ወደ ነበረበት ክልል መመለሱ ሚስና የዜና አገልግሎት ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ ድርጅት ያወጣው መግለጫ በማስደገፍ አረጋገጠ።

ተፈናቃዩ ህዝብ ወደ ነበረበት ይመለስ ዘንድ በተደረገው የግብረ ሠናይ ጥረት፣ ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው ድርጅት፣ የሱዳን መንግሥት ዳግም የማቋቋም እና የትብብር ድርገት የደቡብ ሱዳን የከፊሉ ራስ ገዝ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት በደቡብ ሱዳን የሚያካሂደው ተልእኮ የሚከታተለው የድርጅቱ ጽ/ቤት በጋራ መሳተፋቸው ሚስና አስታወቀ። 60% የተፈናቃዩ ብዛት በሴቶች የተመራ ከ 18 ዓመት እድሜ በታች በሆኑ የክልሉ ዜጎች እና 8% ከ 60 ዓመት በላይ በሆኑት ዜጎች የተሸፈነ እንደሆነም ሚስና አረጋገጠ።







All the contents on this site are copyrighted ©.