2010-03-12 13:53:19

የክህነት ዓመት ዓወደ ጥናት


እዚህ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ ዘንድሮ የክህነት ተዓመት ተብሎ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን እንዲከበር ቅዱስ አባታችን “የካህን ታማኝነት በክርስቶስ ታማኝነት ሱታፌ” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ እንዲከበር RealAudioMP3 ያስተላለፉት ውሳኔ፣ ቲዮሎግያዊ ገጽታውን የሚዳስስ ዓውደ ጥናት ትላትና መጀመሩ ተገለጠ። የአውደ ጥናት ተጋባእያን ዛሬ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ዓ. በነዲቶስ 16ኛ ጋር መገናኘታቸውም የቅድስት መንበር መገልጫ ያረጋገጣል።

በዚህ ዓውደ ጥናት በጀርመን የራትሶቦና ሰበካ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ገራርድ ሙይለር በመሳተፍ አስተምህሮ እቅርበዋል። የካህን ማንነት መለያ ወንጌል አብሣሪ የነፍሳት እረኛ የሚለው ቢሆንም፣ ከተጨባጩ አለም ያልተገለለ፣ ከአለማውያን ምእመናን ጋር የሚወያይ የሚገናኝ ከወቅቱ ባህል ጋር የሚነጻጸር ባህሎች እሰይታዎችን ለማሰናከል የሚያቀርቡት አሳሳች ትምህርቶች ብቃት ባለው በእምነት በቃል እና በሕይወት ምስክርነት የተሸኘ አጥጋቢነት ባለው ቲዮሎግያ ምላሽ እንዲሰጥ የተጠራ ነው።

የካቶሊክ ትምህርት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዜኖን ግርቾለውስኪ፣ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር፣ እድገት የማያሳይ ወደ ኋላ እያዘገመ ነው በማለት ካህን መንፈሳዊ ሰብአዊ ሕይወቱ ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ ወደ ላይ እያቀና ለፍጽምና ሕይወት በጸሎት የሚተጋ በእግዚአብሄር ጸጋ ተደግፎ ወንጌልን በቃል እና በሕይወት ለመኖር ጥረት የሚያደርግ ነው። ባለበት የሚሄድ ካህን በክህነት ጥሪው እየጎደለ ይሄዳል። በዚህ አኳያ በተለያዩ ፈተናዎች ወጥመድ ሥር ይገባል። ስለዚህ የክህነት ማዕርግ የተቀበለ ቀዋሚ እና ቀጣይ የሕንጸት መርሃ ግብር ሊቀርብለት ይገባል። ይህ መርሃ ግብር በሁሉም ካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን ሰበካዎች የሚፈጸም መሆን አለበት ብለዋል።

በመቀጠል የክህነት ጉዳይ የሚንከታተለው ቅዱስ ማህበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ሁመስ እና በጳጳሳዊ አልፎንሲያና መንበረ ጥበብ የቲዮሎግያ መምህር ረአል ትረምብላይ አስተምህሮ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ ክህነት ይላሉ ብፁዕ ካርዲናል ሁመስ፣ በክርስቶስ ሊቀ ካህናት ላይ የጸና መሆን አለበት ስለዚህ ማንኛውም ካህን፣ የክህነቱ የላቀውን አድማስ መቼም ቢሆን መዘንጋት የለበትም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.