2010-03-12 13:54:42

ብፁዕ ካርዲናል ሾንቦርን “የክህነት የድንግልና መሓላ”


የቪየና ሰበካ ቃል አቀባይ አባ ኤሪኽ ላይተንበርገር የቪየና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሾንበርን የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ቤተ ክርስያን የክህነት የድንግልና ጥሪ እጥያቄ ውስጥ አላስገቡም እንዳሉ ካትፕረስ የተሰኘው የካቶሊክ RealAudioMP3 ቤተ ክርስትያን የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።

በቅርቡ ብፁዕ ካርዲናል ሾንበር አንዳንድ ካህናት ባንዳንድ ለአቅመ አዳም ባልደረሱት ላይ ፈጽመውታል የሚባለው የወሲብ ወንጀል በተመለከተ መግለጫ ሲሰጡ፣ እነዚህ ካህናት የዚህ ወንጀል ተጠያቂዎች፣ ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ መስጠት የሚገባቸው ቢሆንም፣ ለዚህ ዓይነት ወንጀል የገፋፋቸው መሠረታዊው ምክንያት መጠናት አለበት፣ ድርጊቱ ጸያፍ ከባድ ወንጀል ነው እንዳሉ የሚዘከር ሲሆን፣ ንጽሕና እና ድንግልና ከሰብአዊ ሕንጸት ጋር ሳይነጣጠል በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤቶች ጥልቅ ትምህርት እንደሚያሻው ይህ ዓይነቱ ወንጀል እንዳይፈጸም ካህን ይሁን ዓለማዊ ምእመን ምን ያክል ጥረት ያደርጋል? ይህ በሕጻናት ላይ የተፈጸመው ወንጀል በተለያየ መልኩ በኅብረትሰብ ዘንድ የሚፈጸም መሆኑ ማመልከታቸው ኣባ ኤሪኽ ላይተንበርገር በማረጋገጥ፣ ብፁዕ ካርዲናል ሾንቦርን የሰጡት መግለጫ የካህን የድግልና መሓላ እጥያቄ ውስጥ አስገባ ተብሎ የሚነዛው ዜና አስተባብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.