2010-03-12 13:50:54

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቶሪኖ ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር


የቶሪኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሰቨሪኖ ፖለቶ ትላትና ጧት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በቶሪኖ የሚያካሂዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር በዝርዝር ጋዜጣዊ RealAudioMP3 መገልጫ በመስጠት እንዳመለከቱት፣ ቅዱስነታቸው በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጥር ልክ ከጠዋቱ 03.15 ቶሪኖ ከተማ በሚገኘው ሳን ካርሎ አደባባይ ከከተማይቱ የመንግሥት ተወካዮች እና የቶሪኖ ከተማ መስተዳድር አባላት እና የከተማይቱ ሕዝብ አቀባበል ይደርግላቸዋል። በመቀጠል ልክ 04.00 ሰዓት መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው የሰማይ ንግሥት ጸሎት እንደሚያሳርጉ ተረጋግጠዋል።

በከተማይቱ ከፒዮሞንተ ብጹዓን ጳጳሳት ጋር በመሆን በሚቀርብላቸው የምሳ ግብዣ ተሳትፈው፣ እዛው በሳን ማርኮ አደባባይ ልክ ከሰዓት በኋላ 10.30 ላይ ከፒዮሞንተ ወጣቶች ጋር ተገናኝተው በ 11.15 ሰዓት የቶሪኖ ዋና ርእሰ ሰበካ ካቴድራል በመጎብኝተው በካቴድራሉ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የቅዱስ ቁርባን ያስተንትኖ ጸሎት ይፈጽማሉ። የክርስቶስ ስቃይ የሕዝቦች ስቃይ በስተሰኘው ርእስ ሥር የተመራ ክርስቶስ የተከፈነበት ጨርቅ የቶሪኖ ከፈን በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል ባለበት ጨርቅ ፊት ያስተንትኖ ጸሎት ከፈጸሙ በኋላ በ 12.15 ህሙማን ለመጎብኘት ትንሿ ቤት ተብላ ወደ ምትጠራው የኮቶሌኞ ቤት የህሙማን መጠለያ ማእክል ይሄዳሉ፣ ኣዛው በኮቶለኒያኒ ማህበር አለቃ ኣባ አልዶ ሳሮቶ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ንግግር አሰምተው በ 01.00 ሰዓት ወደ ቫቲካን እንደሚነሱ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.