2010-03-10 13:35:43

የጸሎት ድጋፍ ለቅድስት መሬት ማኅበረ ክርስትያን


የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ መላይቱ ቤተ ክርስትያን ቅድስት መሬት ትደገፍ ዘንድ ያቀረቡት ጥሪ ከሁሉም አወንታዊ ምላሽ እያገኘ መሆኑ ተረጋገጠ። RealAudioMP3

እልባት ያጣው የእስራኤል እና የፍልስጥኤም ግጭት የቅድስት መሬት ክርስትያን ማኅበረሰብ ክልሉን ለቆ እንዲሰደድ እያስገደደ መሆኑ የጠቀሱት ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ፣ ለዚህ ክልሉ ማህበረ ክርስትያን እንዲጸለይ እና ተግባራዊ ግብረ ሠናይ ይቀርብለት ዘንድ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት ሲገለጥ። በቅድስት መሬት የእንተ ልእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ሥፍራን እና ንብረት አስተዳዳሪ ኣባ ፔርባቲስታ ፒዛባላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅድስት መሬት አለ ክርስትያን ማኅበረሰብ ክርትያናዊ ገጽታው እና ተጨባጩ ታሪክዋ እንደሚሰረዝ እስረድተው፣ የዚህ ክልል ክርስትያን ማኅበረሰብ በቅናት ክርስትያናዊ እምነቱን አቅቦ በመኖር የቤተ ክርስትያን ጥንታዊነት ምስክር በመሆን ሰላምን የሚኖር ሰላምን የሚያነቃቃ ነው። የዚህ ክልል ክርስትያን ማኅበርሰብ በሚታየው የሰላም እጦት ሳቢያ ለዘርፈ ብዙ ችግር መጋለጡ በማስታወስ ሁሉም ለዚህ ክልል ሕዝብ በተለይ ደግሞ ለክርስትያን ማኅበረሰብ ይጸልይ ዘንድ አደራ ብለዋል።

በፖለቲካው መድረክ የክልሉ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ከልቅ ብሔራው ጥቅም ተለቆ ሰላም የሚያስቀድም ለሕዝቦች ሰላም ያለመ መሆን አለበት፣ በሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው ግኑኝነት የሰላም መሠረት መሆኑ በመዘከር፣ ህዝቦች እንዲቀራረቡ በሰላም እንዲኖሩ ከተፈለገ የሰላሙ ሂደት የፖለቲካው መድረክ ጥርት ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች ጥረት ጭምር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.