2010-03-10 13:39:57

አውስትራሊያ፣ የክህነት መበራከት

 


ፊደስ የዜና አገልግሎት የሲድነይ ሰበካ ያሰራጨው ዜና በመጥቀስ በአውስትራሊያ የዘርአ ክህነት የገዳማውያን ተማሪዎች ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱ በመግለጥ በአገሪቱ የክህነት ጥሪ እየተበራከተ RealAudioMP3 መሆኑ አስታውቀዋል።

በዚህ የክህነት ዓመት በመከበር ላይ ባለበተ ወቅት እግዚአብሔር ለአውስትራሊያ ቤተ ክርስትያን የጥሪ ጸጋ በመለገስ፣ ወጣቶች ለክህነት ለገዳማዊ ሕይወት ጥሪ ልባቸው እንዲከፍቱ እያነቃቃ ነው። በሲድነይ ሰበካ እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ስድስት ዲያቆናት ከብፁዕ ካርዲናል ጆርገ ፐል እጅ የክህነት ማእርግ እንደሚቀበሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።

ሌሎች በአገሪቱ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በመማር ላይ የሚገኙት ሁለት የኡጋንዳ ዜጎች መሆናቸው ሲገለጥ፣ በኡጋንዳ የክህነት ማዕርግ ተቀበለው በአውስትራሊያ ልኡካነ ወንጌል በመሆን ሓዋርያዊ አገልግሎት እንደሚፈጽሙ ለማወቅ ሲቻል። እ.ኤ.አ. ከ 1980 ዓ.ም. ወዲህ በአውስትራሊያ ይታይ የነበረው የጥሪ ግሽበት እየተወገደ መምጣቱ ኣባ ኤንቶንይ ፐርስይ በሲድነይ የመልካም እረኛ ማህበር ተማሪዎች አለቃ በማብራራት፣ የጥሪው መበራከት በአውስትራሊያ የተከበረው እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በያመቱ የምታዘጋጀው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ያሰጠው ጸጋ ነው በማለት እ.ኤ.አ. መጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የጥሪ ቀን ተብሎ በአውስትራሊያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንደሚከበር መግለጣቸውም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.