2010-03-10 13:32:16

ብፁዕ አቡነ ሚሊዮረ፣ በዓለም የሴቶች ሁኔታ


እ.ኤ.አ. መጋቢት 8 ቀን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት ኒው ዮርክ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጽሕፈት ቤት የሴቶች ሁኔታ በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው 54ኛው ክፍለ ጉባኤ፣ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት RealAudioMP3 በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ቸለስቲኖ ሚሊዮረ፣ ባለፉት 15 ዓመታት በትምህርት በሙያ እና በሕንጸት ረገድ የሴቶች እኩልነት ለማርገጥ የተደረገው ጥረት አቢይ ውጤት ማስገኘቱ ገልጠው፣ ድኽነት ለመንቀል ሕንጸት ማነቃቃት የማያሻማ ዓላማ መሆን እንዳለበት በማስገንዘብ፣ በፖለቲካው እና በማኅበራዊው ጉዳይ የሴቶች ተሳትፎ በበለጠ ሊነቃቃ ያለበት ጉዳይ ነው ብለዋል።

በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች ብዙ ሴቶች አሁንም ተጨቁነው፣ ጽንስ ለማስወረድ አደጋ ተጋልጠው፣ ተገለው ለሴቶች ተገቢነት ያለው የሕክምና አገልግሎት እጥረት ለፍትወት ሥጋ መሣሪያ እንዲሆኑ በወንጀል ቡድኖች መታደን ምክንያት ለሰብአዊ ስነ አእምሮአዊ እና ማኅበራዊ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ በመጥቀስ፣ ለነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል የሚሰጠው ድጋፍ እና ሕንጸት ካለበት በበለጠ አይሎ መቅረብ አለበት ብለዋል። የኤይድስ በሽታ የመሃይምነት የሥራ አጥነት ችግር በስፋት ሰለባ የሆኑት የሴቶች መሆናቸውም ጠቅሰው፣ ስለዚህ ይህ ሁሉ የዘረዘሩት የሴቶች ሁኔታ ስለ ሴቶች የሚሰጠው ድጋፍ ትብብር እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ እንዲጎለብት የሚያሳስብ ግብረ ገባዊ ግዴታ መሆኑ አብራርተው፣ በመጨረሻ እ.ኤ.አ. በ 1995 ዓ.ም. በፔኪንግ የተካሂፈደው ጉባኤ የሴቶች መብት እና ፈቃድ በተመለከተ ያረቀቀው መሠረታዊ ሰነድ በማስታወስ፣ ቅድስት መንበር እና የተለያዩ የካቶሊክ ተቋሞች ለሴቶች የሚሰጡት ትኵረት ከፍተኛ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.