2010-03-08 13:35:44

የክህነት ዓመት ዓምድ


በፓፑዋ አዲሲቷ ጊኒ እ.ኤ.አ. ከ 2003 ዓ.ም. ጀምረው ሓዋርያዊ አገልግሎ በመስጠት ላይ የሚገኙት የዚህ የተልእኮ ማኅበር በአዲስቷ ጊኒ ወኪል ኢጣሊያዊ የጳጳሳዊ የስብከተ ወንጌል ማህበር አባል ኣባ ጆርጆ ሊቺኒ RealAudioMP3 ፣ ዘንድሮ በመከበር ላይ ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት ስለ ጥሪአቸው በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ገና የ11 ዓመት ዕድሜ ወጣት እያሉ ወንጌላዊ ልኡክ ለመሆን ይመኙ እንደነበር ገልጠው፣ ይኸንን በውስጣቸው ይብሰለሰል የነበረውን ፍላጎት ሳያገሉ፣ ትምህርታቸው እለታዊ ኑሮአቸው በዚህ ላይ ባተኮረ መንገድ በመኖር እና በመታነጽ እ.ኤ.አ. በ 70 ዎች ዓመታት ይኖሩበት በነበረው ቁምስና ከተለያዩ አገር ይመለሱ የነበሩት ልኡካነ ወንጌል ይሰጡት የነበረው ምስክርነት በማዳመጥ፣ ለቤተ ክርስትያን እና ለወንጌል የነበራቸው ፍቅር ከቀን ወደ ከፍ እንዳደረገው በማብራራት፣ ይኸው እ.ኤ.አ. በ 1986 ዓ.ም. በቤርጋሞ የክህነት ማእርግ ተቀብለው በ 1991 ዓ.ም. ወደ ፊሊፒንስ ተልከው በማገልገል ላይ እያሉ፣ በ 2003 ዓ.ም. ወደ ፓፑዋ አዲሲቷ ጊኒ ተልእከው እንዲያገለግሉ ተወስኖ ይኸው በዚህች አገር የጳጳሳዊ የስብከተ ወንጌል ማኅበር ተጠሪ በመሆኑ በአስፍሆተ ወንጌል በሰብአዊ እና በመንፈሳዊ ሕንጸት ዓላማ ተሰማረተው እንደሚገኙ አብራርተዋል።

ካህን ለሕዝብ ቅርብ ከሕዝብ ጋር የሚኖር የሕዝብ አካል መሆን፣ የሕዝብ ዕጣ ዕድል ተካፋይ መሆን አለበት በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.