2010-03-08 13:41:21

የኢራቅ ሕዝባዊ ምርጫ ሂደት


በኢራቅ የሳዳም ሁሴን የመንግሥት ከተገረሰሰበት እለት ወዲህ ሕዝብ የሚወክለውን አካል ለመምረጥ ትላንትና ድምጽ መሰጠቱ ሲገለጥ፣ የምርጫው ሂደት በተለያዩ በዛቻ እና በጥቃት ተግባር የተሸኘ RealAudioMP3 እንደነበር ለማወቅ ተችለዋል።

ምንም’ኳ የመራጩ ህዝብ በጠቅላላ የአገሪቱ ህዝብ ደህንነት እና ጸጥታ ዋስትና ለመስጠት ሰፊ የቁጥጥር ሥነ ሥርዓት ቢከናወንም ቅሉ፣ ሕዝብ ድምጽ ለመስጠት በመመዘጋጀት ላይ እያለ በተከታታ ጥቃት መጣሉ ተረጋግጠዋል። የምርጫው ሂደት በኢራቅ ሰዓት አቆታጣር ከሰዓት በኋላ ልክ 11 ሰዓት ላይ መጠናቀቁ ሲነገር፣ የተካሄደው ምርጫ በማስመልከተ የስነ መልክአ ምድር ፖለቲካ ሊቅ ሚላኖ ከተማ በሚገኘው የካቶሊክ መንበረ ጥበብ መምህር ሪካርዶ ሬዳኤሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ በ2005 ዓ.ም. ተካሂዶ ከነበረው ሕዝባዊ ምርጫ ይህ ትላትና የተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ዒራቃዊ ምርጫ ነበር ብለዋል። የሳዳም ሁሴን ሥርዓት በተገረሰሰበት ማግሥት እና ቀጥሎ የታየው ውጥረት ሻል ባለበት ወቅት የተካሄደ በአገሪቱ የሚገኙት የተለያዩ ጎሳዎች ሃይማኖቶች እና የፖለቲካ ሰልፎች ያሳተፈ፣ ዴሞክራሲያዊ ቅርጽ ያለው ነው ብለዋል።

300 የተለያዩ የፖለቲካ ሰልፎች በተለያየ ፖለቲካዊ መርሃ ግብር ጣምራ በመፍጠር ማእከላዊ መንግሥት ለማጠናከር፣ የሕዝብ ጸጥታ እና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ በሚሉትን እና በሌሎች ሌሎች ፖለቲካዊ እቅዶች መሠረት ጣምራ የፈጠሩ ቢሆንም፣ የፖሊቲካ ሰልፎች ቁጥር መብዛት የሕዝብ ድምጽ እንዲሚከፋፍለው እና በሙሉ ድምጽ አብላጫ የሚሆን የፖለቲካ ሰልፍ እንዳይኖር የሚያደርግም ነው። ስለዚህ ይህ ዓይነቱ አሠራር ሰፊ ድምጽ የሚያግኙት ውህደት የፈጠሩት የፖለቲካ ሰልፎች ለመምራት እንዲችሉ መግባባት ይኖርባቸው፣ ስለዚህ ይህ አይነቱ የአመራር ሥርዓት፣ ለአገሪቱ ደህንነት እና ጸጥታ ፈታኝ ነው ብለዋል።

በመጨረሻ የተለያዩ የአገሪቱን ንኡሳን ጎሳዎች እና ሃይማኖቶችን ጸጥታ እና ደህንነት ዋስትና ለመስጠት ሁሉም የፖለቲካ ሰልፎች ቃል ቢገቡም ቅሉ ጥንታዊው የአገሪቱ ክርስትያን ማኅበረሰብ አገሩን ለቆ እንዲወጣ የሚገፋፋው አመጽ እንደቀጠለ ነው። ስለዚህ ይህ ችግር እንዲወገድ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተሳትፎ እና ድጋፍ ወሳኝ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.