2010-03-08 17:22:23

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐውጾተ ኖልዎ በቅዱስ ዮሐንስ ዘመስቀል ቍምስና


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ዮሐንስ ዘመስቀል ቍምስና ባደረጉት ሐውጾተ ኖልዎ “ሌላ መልእክት እንዳትጠብቁ፣ እናንተ ራሳችሁ ሰባክያነ ወንጌል ሁኑ። መንፈሳዊ ሃኬትን በማስወገድ በማንኛውም ዕለታዊ ተግባራችሁ የኢየሱስ መልእክትን መስበክንና እርሱን መሠረት ማድረግን ለማወቅ ሕያዋን ድንጋዮች በመሆን ቤተ ክርስትያንን ሕነፁ” ሲሉ ተማጥነዋል።

ቅዱነታቸው መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ብፁዕ ካርዲናል ኣጎስቲኖ ቫሊኒ አብረዋቸው ነበር፣ ክቅዳሴ በኋላም ከቍምስናው ምክር ቤት ጋር ተገናኝተው እንደተወያዩ የቫቲካን ዜና አመልክተዋል።

በቅዳሴው ባሰሙት ስብከት “ጌታ ንስሐ ግቡ መንግሥት ሰማያት ቅርብ ነው” ያለውን ወንጌል ከማንበባችን በፊት በቀረበን ምስማክ አዳምጠናል። በሥርዓተ አምልኮአችን ዘመነ ጾም ከሁሉም የበለጠ የጸጋ ጊዜ ነው። በዛኤው ወንጌል የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ኢየሱስ ንስሐ የማይገባ ይጠፋል ሲል በሰሊሆም ግንብ ተደርሞሶባችው የሞቱት አሥራ ስምንት ሰዎች በማውሳት በእነዚህ ሰዎች የደረሰውን ነገር እንደ ኃጢኣት ቅጣት ለተረጐሙት ሰዎች “እነዛ ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ የባሱ ኃጢአተኞች ይመስላችኋልን ፣ አይደለም! በኃጢኣአታችሁ ተጸጽታችሁ ንስሐ ባትገቡ እናንተም እንደእነርሱ ትጠፋላችሁ እላችኋለሁ” ሲል ዘመነ ጾምን ለንስሐ እንድንጠቀምበት ጥሪ ያቀርብልናል፣ በዘመነ ጾም እያንዳንዳችን በምናደርገው ጸሎት በምናራምደው ሕይወት ከሊሎች ጋር ባለን ግኑኝነት ያልተስትካከለውን በማስተካከልሁሉን ማሳደስ እንዳለብን ያስጠነቅቃል። ኢየሱስ ይህንን ጥሪ የሚያቀርብልን እንደ ቅጣት ሳይሆን ለደስታችንና ለደኅንነታችን ጥቅም እንድናውለው ብሎ ነው። ወንጌሉ የሚያስተምረው ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ነው፣ ይህንን ምሕረት ለማግኘት ሳንውል ሳናድር በንስሐ ወድ እግዚአብሔር መመለስ እንዳለብንና ሕይወታችን ማሳደስ እንዳለብን ያመለክታል። ፍሬ በማታፈራው የበለስ ዛፍ ምሳሌ በእርሻው ዋናና በአትክልተኛው መህከል በሚደረገው ውይይት በአንድ በኩል የእግዚአብሔር ምሕረትና ትዕግሥት ለንስሐ ጊዜ መስጥቱ በሌላው በኩል ደግሞ ውሳጣዊ ለውጥና ንስሐ በግልጽ እንደሚያስፈልግ ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስም ወደ ቆሮንጦስ ስዎች በጻፈው በአንደኛ መልእክቱ ምዕራፍ 10 ላይ የሙሴ ተባባሪዎች አንድ ዓይነት መንፈሳዊ ምግብ እንደተመገቡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር በአብዘኛዎቹ አለመደሰቱና ሬሳቸው በበረህ ውድቆ መቅረቱን በማመልከት የማስጠንቀቂያ ምሳሌነት ይሰጠናል።

ውድ የቅዱስ ዮሐንስ ዘመስቀል ቍምስና ምእመናን በመሃከላቸው መገነቴ ደስ ይለኛል፣ የእግዚአብሔርን ቀን ከእናንተ ጋር መቀደሴ ደስ ይለኛል፣ ሲሉ ካርዲናሉና ምእመናኑን ሰላ በማለት የላቀ ሰላምታቸውን ለሁሉም አቅርበዋል።

ከቅዳሴ በኋላ ከቍምስናው ምክርቤት አባሎች ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል ከሰጡና ከተወያዩ በኋላ የተለመደውን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ለመምራት ወደ መንበራቸው መንበረ ጴጥሮስ ተመልሰው እኩለ ቀን ላይ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺ ለሚገመቱ ምእመናን የዕለቱን ቃለ ወንጌል በማመልከት በዚሁ ሦስተኛው የጾመ አርባ እህድ ጌታ ለንስሐ እንደሚጠራን አስታውሰው ተመሳሳይ ትምህርት ሰጥትዋል። ትምህታቸውም እንደሚከተል ነበር። “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦ የዛሬው የጾመ አርባ ሦስተኛ እሁድ ሥርዓተ አምልኮ የንስሐ መግባት አርእስት ያቀርብልናል። የመጀመርያው ንባብ ከኦሪት ዘፀዓት ሦስተኛ ምዕራፍ የተወሰደ ሙሴ በጎችን እየጠበቀ አንድ ቍጥቋጦ በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ። ሙሴም ይህንን አስደናቂ ነገር ለማየት ወደሚቃጠለው ቍጥቋጦ ይቀርባል፣ እግዚአብሔር ከቍጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ። ሙሴ፥ ሙሴ ሆይ አለ። እርሱም። እነሆኝ አለ። ወደዚህ አትቅረብ፤ አንተ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ አለው።ደግሞም። እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ አለው። ሙሴን። <<ያለና የሚኖር>>እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። <<ያለና የሚኖር>>ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።” እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ህይወት በተለያዩ ሁኔታዎች ይገለጻል። በሕይወታችን የእግዚአብሔርን መኖር ለማወቅ ከፈለግን በትሕትና እንቅረበው፣ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ይህም እኛን ለማሳመን የተፈጸመ ነው። ይህም እግዚአብሔር ለድኃና ለትሑት እንደሚገለጽ ያመለክታል፣” ሲሉ ቃለ ወንጌሉን በሚመለክት በቅዱስ ዮሐንስ ዘመስቀል ያሰሙትን ስብከት የሚመሳሰል ትምህርት ሰጥተው ምእመናኑን በተለያዩ ቋንቋዎች አመስገነው ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ትምህርታቸውን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.