2010-03-08 13:34:33

ሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ፦ የተገባ እና የታረመ ሚሥጢረ ኑዛዜ


የተገባ እና የታረመ የሚሥጢረ ኑዛዜ አሠራርና አና አስተዳደር በሚል ርእስ ሥር የተመራ ለካህናት በተለይ ደግሞ ለወጣት አዳዲስ ክህናት ያቀና ሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ ያዘጋጀው የትምህርት ፕሮግራም ዛሬ ቫቲካን በሚገኘው ጳጳሳዊ RealAudioMP3 የበላይ ፍርድ ቤት ሕንጻ መከፈቱ ከቅድስት መንበር የተላለፈልን ዜና ያረጋገጣል።

ይህ በሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ አቢይ አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ፎርቱናቶ ባልዘሊ የሚመራው የትምህርት መርሃ ግብር እ.ኤ.አ. እስከ መጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲሚቀጥል ሲገለጥ፣ የሚካሄደው አውደ ጥናት እና የሚሰጠው ትምህርት፣ ሚሥጢረ ኑዛዜ በካቶሊክ ግብረ ገብ እና ሕገ ቆኖና ላይ ያተኮረ ሆኖ ለኑዛዜ የሚቀርቡት የሚናዘዙት ወይንም ተናዛዡ ምኅረት የሚጠይቅባቸው ሐጢኣቶች በቤተ ክርስትያን አማካኝነት ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ምህረት እና በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቤተ ክርስትያን የምትሰጥበት ውሳኔ በጥልቀት በመመልከት፣ በተደጋጋሚ አሻሚ ሆነው የሚገኙት ሚሥጢረ ንስሐ ለጥያቄ የሚያስገቡ ጉዳዮች፣ የአንዳንድ ሐጢአቶች መመዘኛዎች በተጨማሪም ሚሥጢረ ንስሓ ስለ ሚሥጢረ ተክሊል የሚከተለው ግብረ ገባዊ መመዘኛ ለመለየት ይኸንን ጉዳይ በተመለከተ ካህን ሚሥጢረ ንሰሐ በማስተዳዳሩ ረገድ መከተል የሚገባው የተገባ እና የታረመ አሠራር በጥልቀት የሚብራራበት እንደሚሆን ከሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ የተላለፈል መገልጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.