2010-03-05 13:58:14

ፓኪስታን፣ ጸረ ክርስትያን ተግባር


ፓኪስታን ከአፍጋኒስታን በሚያዋስናት ቤሉኪስታን ክፍለ ሃገር በምተገኘው የቁኤታ ከተማ የሳሊዚያን ማኅበር ያቋቋመው እና የሚያስተዳድረው የትምህርት ማእክል የዛሬ አንድ ወር በትክክል እ.ኤ.አ. የካቲት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. 8 የጦር መሣሪያ RealAudioMP3 በታጠቁ ሰዎች ከባድ ጥቃት እና የዘረፋ አደጋ በማድድረስ በዚህች ከተማ የውጭ አገር ዜጎች እንዳይኖሩ የሚያሳስብ የዘረኝነት መልእክት ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት በመጠቆም፣ ከዚያኑ ዕለት ጀመሮ ጸረ ክርስትያን ያቀና የዘረኝነት ተግባር በዚሁ ክልል እየተስፋፋ መምጣቱም የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።

በትምህርት ቤት አገልግሎት ከሚሰጡት የሳሊዚያን ማኅበር አባላት ውስጥ አንዱ ከባድ የስነ አእምሮ ተጽእኖ ደርሶባቸው ከአገሪቱ ለመውጣት መገደዳቸው እና የተቀረቱ ገዳማውያን ዕለታዊ አገልግሎታቸው ፈጽመው ለአዳር በከተማይቱ ወደ ሚገኘው ወደ ሓዋርያዊ ኅየንተ ሕንጻ እንደሚሄዱ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ። የተጣለው አደጋ ተጠያቂ አክራሪያ ሙስሊሞች ወይንም የቤሉኪስታ የነጻነት ግንባር እንዱሁም የክልሉ የወንጀል ቡድኖች ይሁኑ ገና በውኑ የታወቀ ነገር የለም። በዚህች ከተማ የሳሊዚያን ልኡካን አለቃ ኣባ ኤሪክ ኤንግለት የተጣለው ጥቃት እጅግ አሳሳቢ የዘረኝነት መልእክት ያለው መሆኑ በመጥቀስ፣ በትምህርት ቤቱ አለ ሃይማኖት ልዩነት ለሁሉም አገልግሎት እንደሚሰጥ፣ በክልሉ ያለው 70% የመሃይምነት ችግር ለማጥፋት ያለመ መሆኑም በማስረዳት፣ ትምህርት ቤቱ ማእከልም 50 ሕፃናት በአዳሪነት የሚንከባከብ፣ 1.300 ተማሪዎችን የሚያስተናግድ 60 አስተማሪዎች እንዳሉትም አባ ዛጎ በማብራራት በዚህች ከተማ የሳሊዚያን አገልግሎት እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. የጀመረ መሆኑም ማሳወቃቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.