2010-03-05 13:56:45

ፋሉጃ፣ የ2004 ዓ.ም. የቦብ ጥቃት ጠባሳ


ባለፉት ቀናት እ.ኤ.አ. በ 2004 ዓ.ም. በኢራቅ ፋሉጃ ከተማ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የመከላከያ ኃይል በጣሉት ጥቃት የተጠቀሙበት የጦር መሥሪያ እና የፈጸሙት የቦምብ ድብደባ በክልሉ በሰው ላይ ያስከተለው RealAudioMP3 ጉዳት፣ ገና በሕጻናት ላይ የቅርጸ ኣካላዊ እና ስነ ኣእምሮአዊ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ ስለ ተጣለው አደጋ ጉዳይ የሚያጣራው ድርገት በመጥቀስ ቢቢሲ ያሰራጨው ዘገባ፣ እጅግ እያከራከረ መምጣቱ ሚስና የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።

በፋሉጃ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት አየር ኃይል የጣሉት ጥቃት ማብቅያ ማግሥት፣ ጋዜጠኛ ጆን ሲምፖስን እያካሄዱት ባለው ዘገባ፣ በዚህ ክልል ከሚወለዱት ሕጻናት ውስጥ በሺሕ ይሚገመቱ ሕፃናት አደገኛ የጤና መታወክ ያለባቸው ሆነው እንደሚወለዱ እና አንዳንዶቹ ከተወለዱበት ልክ በሁለተኛው አሊያም በሶስተኛው ቀን ከዚህ ዓለም በሞት እንደሚለዩ ይጠቁማል።

የዚህ ሁሉ ጠንቅ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የጠጠቀሙበት የጦር መሣሪያ እንደሆነም ቢቢሲ የድርገት የምርምር ውጤት በማስደገፍ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.