2010-03-05 13:55:17

ኢራቅ፣ ጸረ ሕዝባዊ ምርጫ ያቀና ጥቃት


በኢራቅ እ.ኤ.አ. እፊታችን እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ሕዝባዊ ምርጫ እንደሚካሄድ ሲገለጥ፣ የምራጫው ሂደት ላደጋ የሚያጋልጡ የአሸባሪያን ጥቃት እሁንም እያንዣበበ ነው። ትላትና በጥቂት የሰዓታት RealAudioMP3 ልዩነት ውስጥ ሶስት የጥቃት አደጋ መጣሉ ሲገለጥ፣ የመጀመሪያው የቦምብ ጥቃት በአንድ የድምጽ መስጫ ጣቢያ ቀጥሎ በሌሎች በሁለት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ያጥፍተህ ጥፋ አደጋ መጣሉ ከኢራቅ የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

በተጣለው ጥቃት ሳቢያ አራት ሕፃናት የሚገኙባቸው 12 ሰዎች ለሞት አደጋ መጋለጣቸው ሲነገር፣ ትላትና በባቁባ በተጣለው ሶስት ያጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ 30 ሰዎች ለሞት ዳርገዋል። እሁድ የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ በሚያስተናግዱት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ባሉበት ክልል እየደረሰ ያለው ጥቃት፣ ሕዝብ ድምጽ ለመስጠት ያለው ፍላጎት የሚቀጭ እንዳይሆንም ያሰጋል። ይህ በንእንዲህ እንዳለ የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ በኢራቅ የዲሞክራሲ ሥርዓት መሥፈን ምልክት ነውን ለሚለው ጥያቄ በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ በሚገኘው መንበር ጥበብ የአለም አቀፍ ግኑኝነት ጉዳይ መምህር የስነ ፖለቲካ ሊቅ አሌሳንድሮ ኮሎምቦ ከቫቲካን ሬዲዮ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፦ ሕዝባዊ ምርጫ ለዲሞክራሲው ሂደት መሠረት ቢሆንም ቅሉ፣ ለብቻው ለዲሞክራሲ መረጋገጥ በቂ ክንዋኔ አይደለም። ይህ ሕዝባዊ ምርጫ ኢራቅ እንደ አገር እና መንግሥት ገና መረጋገጥ እና መገንባት በሚያስፈልግባት ወቅት የሚካሄድ ነው፣ ሕዝባዊው ምርጫ የሚቃወሙ አደገኛ የጥቃት ምልክት እጅግ እየተስፋፋ ነው፣ ሆንም እጅግ አሳሳቢው ጉዳይ ከምርጫው በኋላ የሚለው ጥያቄ ነው ብለዋል። ምክንያቱም ይላሉ በዚህች አገር በተለያዩ ጎሳዎች መካከል ያለው ውጥረት አሁንም እንደጸና ነው። በአገሪቱ የተከሰተው መከፋፈል እና ልዩነት ለመጠገን እየተከናወነ ያለው ፖለቲካዊ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ መርሃ ግብር፣ ገና እፍጻሜ ላይ ባለ መድረሱ ሊረጋገጥ የሚፈለገው የዴሞክራሲው ሥርዓት የዚህ የተጠቀሰው ግና መፈጸም ያለበት መርሃ ግብር ውጤት ስለ ሚሆን፣ የዴሞክራሲው ሂደት አሳሳቢ ነው ብለዋል።

የአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለመሆን ለምርጫው የቀረቡት አንዳንድ አካላት ከቀድሞ የሳዳም ሁሴን መንግሥት ማለትም ከባአት ብቸኛው የፖለቲካ ሰልፍ ግኑኝነት ነበራቸው ወይንም አባላት ነበሩ በሚል ክስ፣ የእጩነት መብት ተነፍጐአቸዋል፣ ይህ ውሳኔ የሱኒት ሙስሊሞችን እጅግ የነካ ነው፣ ቢሆም የሚካሄደው ምርጫ የሚረጋገጠው ውጤት፣ ኢራቅ ላለችበት ፖለቲካዊ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያው ጉዳይ መመዘኛ ይሆናል። በምርጫው የተሸነፉት የምርጫው ውጤት እና የተካሄደው ምርጫ እንዴት ይቀበሉታል? ላጋጠማቸው ሽንፈት የሚሰጡት ምላሽ ምን ይሆን? የሚል አንገብጋቢ ጥያቄ በሁሉም ዘንድ እያብሰለሰለ ነው በማለት የሰጡትን ጥያቄ አዘል ምላሽ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.