2010-03-03 16:42:55

የጁባ ሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ መልእክት ጻፉ


የጁባ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉኩዱ ሎሮ ከአንድ ወር በኋላ በደቡብ ሱዳን የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክተው ሐዋርያዊ መልእክት መጻፋቸ ሲ ኤን ኤስ የተባለ የዜና አገልግሎት አመልክተዋል።

የመልእክቱ አርእስት “እውነተኛ የሕዝብ ድምጽ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው” ይላል።

የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ለ24 ዓመታት ያህል በውግያ በስደትና በጭቆና ካሳለፉ በኋላ ለመጀመርያ ግዜ እአአ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም የመድብለ ፓርቲዎች ምርጫ ያካሄዳሉ።

ብፁዕነታቸው ምእመናን ተወዳዳሪዎችን በደንብ ማወቅ እንዳለባቸው ሲያመልክቱ “ቤተ በዚህ አስፈላጊ ሂደት ምእመናንዋን በተገባ ለማስተማርና ለማምራት የሞራል ግዴታ እንዳላት” ገልጸዋል።

አያይዘውም “በፈጸምናቸው እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑና ራሳችንን የሚጐዱ ኃጢአቶች በተለይም በደቡብ ሱዳን በተፈጸመው ዓመጽ ማለትም ጐሳ በጐሳ ላይ ማጥቃት መግደል ዓመጽ ምዝበርና ሌሎች ጥፋቶችን ከእግዚአብሔር ይቅሬታ እንጠይቅ። እነኚህን ኃጢአቶችን በጸሎትና በግብረ ሠናይ መካስ አለብን፣” ሲሉ ባለፈው ስለተፈጸመው ዓመጽ ንስሐ እንዲሚያስፈልግ ገልጸዋል። ሕዝቡንና እጮኞቹን አስመልክተው ደግሞ፣ በዚሁ ምርጫ የእያንዳንዳችሁ ድምፅ ምርጫችሁ መሆኑን በመገንዘብ ለጋር በጎ እንድታስቀድሙ አደራ፣ እጨኞችም ከጉቦና ከሙስና ነጻ በሆነ መንገድ አገርን በፍትሕና በእኩልነት ለማስተዳደር እንድትዘጋጁ ሲሉ በ2005 ዓም የተደረሰውን የሰላም ውል እንዲከበር አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.