2010-03-03 16:44:48

ቤተ ክርስትያን የዘር አድልዎ እና ፍትሕ አልባነትን ትቃወማለች


በቅድስት መንበር በስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተዘጋጀ በጂፕሲ የሚታወቁ የኤውሮጳ ዘላን ማኅበረ ሰብ ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮን የሚመለት ዓውደ ጥናት በቫቲካን እየተካሄደ ነው፣ እስከ ነገ ሐሙስም ይቀጥላል። በዓውደ ጥናቱ በኤውሮጳ ጂፕሲዎችን የሚያገልግሉ የየአገሩ የዚህ አገልግሎት ዳይረክተሮች ተሰብስበው እየተወያዩ ነው።

ባለፈው ዜናችን ተጠቅሶ እንደነበረው ጉባኤውን በቅዳሴ የከፈቱት በቅድስት መንበር የስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ ናቸው። እንዲሁም የምክር ቤቱ ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኣጎስቲኖ ማርከቶም ተገኝተዋል።

ብፁዕነታቸው በዓውደ በጉባኤው ባሰሙት ንግግር “ቤተ ክርስይትያን የሰው ልጅ ሕይወት ሰብአዊ እስከሚሆን ድረስ ፍትሕ አልባነት እና የዘር አድልዎን ለማውገዝ የተጠራች ናት። ቤተ ክርስትያን ለጥሪዋና ተልእኮዋ ታማኝ በመሆን ድሆችን በቅንነት ያገለገለች እንደሆነ የኅሊና መርመራ የምታደርግበት ጊዜ ነው። አሳዛኙ የጂፕሲዎች ታሪክና ሕይወት በመነጠልና በስደት የተሞላ ነው። በዚህ ታሪክ ቤተ ክርስትያንም ቀጥተኛን ተዛዋሪ የሆኑ የራስዋ ጥፋቶች አልዋት፣ እነኚህ ጥቂትም ቢሆኑ ያደረጋቻቸውን ትላላቅ ነገሮች ሊያደፍርሱ ይችላሉ። በዕርቅና በፍትሕ ተመርተን ሮም እና ሲንት የሚባሉ ጂፕሲዎች በቤተ ክርስትያን ሕይወትና ሃብት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ቤተ ክርስትያንም በበኵልዋ በመሀከላቸው በመገኘት አገልግሎትዋና አጋርነትዋን እንድታበረክት አደራ” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.