2010-03-01 14:34:53

ፓኪስታን


የምስልምና ሃይማኖትን የሚያረክስ ተግባር ፈጽመዋል በሚል ክስ መሠረት በፓኪስታን ሁለት ክርስትያን ወጣቶች ዓለም በቃኝ ፍርድ እንደተበየነባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አረጋገጠ። የክልሉ ቤተ ክርስትያን በነዚህ ወጣት RealAudioMP3 ክርስትያኖች ላይ የተበየነው ፍትሕ አልቦ ፍርድ እንዲሰረዝ እና ነጻ እንዲለቀቁ የኢስላማባድ እና የራዋልፒንዲ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሪፉን ኤንቶንይ በኩል ጥሪ ማቅረበዋም የዜና አገልግሎቱ አክሎ ያመለክታል።

ዓለም በቃኝ ከተበየነባቸው ውስጥ አንዱ የላሆር ከተማ ነዋሪ ቃማር ዳቪድ የተባለ የክልሉ ክርስትያን ማኅበርሰብ አባል እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. የምስልምና ሃይማኖት አርክሰኻል በሚል ክስ መሠረት፣ ለእስር መዳረጉ እና በእርሱ ምክንያት ክርስትያን ቤተ ሰቦቹም ጭምር ለተለያዩ አደጋ መጋለጣቸው የዜናው አገልግሎት በማስታወስ፣ የተበየነው ፍርድ በክልሉ ጸረ ክርስትያን ያነጣጠረ አላማ እንዳለ የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የወጣቱ ጠበቃ በመግለጥ ባልፈጸመው ወንጀል ለእስር ተዳርገዋል ብለዋል። ሁለተኛው ዓለም በቃኝ የተበየነበት 26 ዓመት ዕድሜ ያለው ኢምራን ማሲህ የፋይሳልባድ ነዋሪ ክርስትያን ቁራን ሲያቃጥል አይቸዋለሁ በማለት ካንድ ጎረቤቱ በተመሠረተበት ክስ ምክንያት እ.ኤ.አ. ከባለፈው ጥር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለእስር የተዳረገ እና ከትላትና በስትያ ዓለም በቃኝ ፍርድ እንደተበየነበት ፊደስ የዜናው አገልግሎቱ ያረጋገጣል።

በፓኪስታን የክርስትና የጥናት ማእከል አስተዳዳሪ ፍራንሲስ ሜህቡድ ሳዳ በሁለቱም ክርስትያን ላይ የተበየነው ፍርድ በአገሪቱ ጸረ ክርስያን ያነጣጠረ እ.ኤ.አ. በ 1986 ዓ.ም. ጀምሮ የተደነገገው ሕግ መሠረት የተወሰነ እና በዚሁ ጸረ ክርስያት ሕግ ምክንያት ብዙ ክርስትያን የአገሪቱ ዜጋ ላደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.