2010-03-01 14:36:00

የክርስትያን አንድነት ለማረጋገጥ


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በተለያዩ ሃይማኖትች መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይት በሚያነቃቃ ድርገት አማካኝነት የጠራው ብሔራዊ አቀፍ ስብሰባ በአንኮና ከተማ ዛሬ መከፈቱ ተረጋገጠ። RealAudioMP3 ይህ በኢጣሊያ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ምእመናን ማእከል ያደረገበየመላ የኢጣሊያ ቁምስናዎች ሥር የሚተዳደሩት የሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ቀስቃሽ ምክር ቤት ተጠሪዎች የጠራው ስብሰባ እ.ኤ.አ. እስከ ፊታችን መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚቀጥል ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይህ የሚካሄደው ስብሰባ ቲዮሎጊያዊ እና ሥነ ቤተ ክርስያናዊ ጥናቶች ማእከል ያደረገ መሆኑ ሲገለጥ፣ ስብሰባው በንግግር የከፈቱት የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዲዮኒጂ ተታማንዚ እና በኢጣልያ የሮማኒያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲሉዋን ስፓን መሆናቸውም ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.