2010-03-01 14:37:09

የክህነት ዓመት፣ የምስክርነት ዓምድ


የእናቴ ብፁዕት ተረዛ ፈለግ በመከተል የመጀመሪያ የዚህ ማኅበር የካህናትየፍቅር ልኡካን ማኅበር አባል የሆኑት እና የዚህ የካህናት ማኅበር ከማድረ ተረዛ ጎን በመሆን የመሠረቱት አባ ጆሰፍ ላንግፎርድ ዘንድሮ በመከበር ላይ RealAudioMP3 ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት የእግዚአብሔር ብዕር በሚል ርእስ ሥር የእናቴ ብፁዕት ተሬዛ ታሪክ የምትገልጥ የደረሱ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እግዚአብሔር እንዴት ለክህነት ጥሪ እንደፈለጋቸው ሲያብራሩ፣ ገና የስድስት ዓመት ዕድሜ እያሉ የተሰማቸው ጥሪ መሆኑ በማስታወስ፣ በሮማ የቲዮሎጊያ ተማሪ ሆነው በቅዱስ ጳውሎስ የደናግል ማኅበር በሚተዳደረው ቤተ መጽሓፍት ገብተው መጽሕፍት በማገላበጥ ላይ እያሉ፣ አንድ የማድረ ተረዛ ስዕል የተቀመጠበት መጽሐፍ አይተው መጽሐፉን ገዝተው ማንበብ እንዳነበቡ እና የማድረ ተረዛ ታሪክ ማርኮአቸው በሳቸው ማኅበር የካህናት ማኅበር የመመሥረት ቅዱስ አላማ በውስጣቸው መቀስቀሱንም አስታውሰው፣ ይህ ቅዱስ ፍላጎት እውን ሆኖ ይኸው የክህነት ጥሪያቸው በዚህ በማድረ ተሬዛ የካኅናት ማኅበር ተረጋግጦ የክርስቶስን ፍቅር በመመስከር ላይ እንደሚገኙ ገልጠዋል።

ከተጠማው ከተናቀው ክርስቶስ ጋር በመገናኘት ለተናቀው ለታረዘው ባጠቃላይ ለሚሰቃየው እና እጅግ በድኽነት ጫንቃ ሥር ወድቆ ለሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል ቅርብ በመሆን ክርስቶሳዊ ሕይወት ለመኖር የተጠራ ማኅበር አባል መሆናቸው በማብራራት ይኽ የፍቅር ተልእኮ ቅዱስ ቁርባን ማእከል ያደረገ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.