2010-03-01 14:33:32

ክርስትያን፣ የቤተ ክርስትያን አባልነት


የሞልዶቫ ረፓብሊክ መራሔ መንግሥት ቭላድ ፊላት ከትላትና በስትያ ከደቡብ ምስራቅ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አባላት ጋር ባካሄዱት ውይይት አናሳ የማኅበርሰብ ክፍል መሆን አናሳው የኅብረተሰብ ክፍል ዝቅተኛ RealAudioMP3 እያደርገውም፣ እንዲሁም አናሳው ማኅበረ ክርስትያን የምትወክል ቤተ ክርስትያን ዝቅተኛ እይደለችም እንዳሉ ሲገለጥ፣ በሞልዶቫ ሬፓብሊክ የቅድት መንበር ወኪል ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስኮ ኻቪየር ሎዛኖ፣ ለደቡብ ምስራቅ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ የቅዱስ አባታችን መልእክት እና ቡራኬ አቅርበዋል።

ይህ በሞልዶቫ በምትገኘው በቺሲኑ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የደቡብ ምስራቅ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጵሳት ጉባኤ እስከ ፊታችን እሁድ እንደሚቀጥልም ሲረጋገጥ፣ የከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶን ኮሳ ቤተ ክርስትያን ለሞልዶቫ ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው አቢይ ድጋፍ ለጉባኤ ባሰሙት ንግግር በመጥቀስ ምስጋናን አቅርበዋል።

በኤውሮጳ ህብረት የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ አልዶ ጆርዳኖ ስለ ጉባኤው በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአንዳንድ የኤወሮጳ አገሮች የምትታየው አናሳ ቤተ ክርስትያን ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለወንጌላዊ ሕይወት እና ለአስፍሆተ ወንጌል ለሚወጠነው እቅድ አብነት ነች ብለው፣ አናሳ መሆን የምትከተለው የካቶሊክ እምነት በበለጠ ለመለየት እና ለመረዳት እንዲሁም አናሳው ካቶሊክ ክርስትያን በበለጠ እንዲደጋገፍ እና ህብረቱን እንዲያጸና የሚገፋፋው እና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ለሚደረገው ውይይት ዋና ተወናያን እንዲሆን የሚያነቃቃው አጋጣሚም ነው ካሉ በኋላ፣ ለወንጌል ታማኝ ለቤተ ክርስትያን እና ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታማኝነት የሚያጎላ ማኅበረ ክርስትያን ነው ብለዋል።

የማኅበረሰብ ማእከል ምን መሆን እንዳለበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሓቅ በተሰኘችው አዋዲት መልእክታቸው መቀራረብ እና መደጋገፍ ከቤተሰብ የሚጀመር ነው ያሉትን ሐሳብ የሚያጎላ ማኅበረ ክርስትያን በመሆኑም፣ የፍቅር ባህል እና የሕይወት ባህል የሚያነቃቃ የማኅበረሰብ ክፍል መሆኑ በማስረዳት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።

የደቡብ ምስራቅ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ ላስተናገደቸው የማልዶቫ ረፓብሊክ ቺሲኑ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶን ኮሳ በበኵላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ስብሰባ የዚህ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አባላት ብፁዓን ጳጳሳት፣ የክልላቸው ቤተ ክርስትያን እና ማኅበረ ክርስትያን በተመለከተ ማኅበራዊ ሃይማኖታዊ እና ፖሊቲካዊ ገጽታ የሚያጎላ ሰነድ ማቅረባቸው በመጥቀስ፣ ችግሮችን ለመፍታት ችግሩን መለየት ተቀዳሚ ሂደት መሆኑ የገለጠበት መድረክ ነው ብለዋል።

የነዚህ አገሮች የፖለቲካ አካላት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሰላም የሰፈነበት ማኅበርሰብ ለማረጋገጥ ለሚደረገው ውይይት እጅግ አስፈላጊ መሆኗ የሚያምኑ መሆናቸውም ብፁዕ አቡነ ኮሳ በመግለጥ፣ የክልሉ ቤተ ክርስትያን ክርስቶስን ለመስበክ ወንጌሉንም ለማዳረስ ተቀዳሚ አላማ መሆኑ በማሳወቅ፣ በዚህ ተልእኮ አቢይ ክንዋኔ እየፈጸመች መሆኗንም ገልጠው፣ በሌላው ረገድ ግብረ ገብ እና ሥነ ምግባር ለአንድ ማኅበረሰብ ሰላማዊ እና ፍትህ የተካነው ሕይወት ማእከል መሆኑ፣ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ትምህርት መሠረት ያደረገ ሕንጸት እንደምታቀርብ በመመስከር፣ የሞልዶቫ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በዚህች አገር የሚታየው ማኅበራዊ ችግር በተለይ ደግሞ ሰዎች ለተለያዩ ክብር ሰራዥ ተግባሮች የሚያጋልጡ የወንጀል ቡድኖች የሚፈጽሙት ጸረ ሰብአዊ ተግባር በመቃወም ለተሟላ ሰብአዊ ክብር መብት እና ፈቃድ መረጋገጥ አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጠች ነው ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.