2010-03-01 14:31:11

ከፍተኛ ታማኝነት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለቁስጥንጥንያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ 70ኛው የልደት ዓመት ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት፣ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ክርስቶስ እንደተመኘው RealAudioMP3 የተሟላ ክርስትያናዊ አንድነት እንዲረጋገጥ በሚያደርጉት የጋራው ጉዞ የእግዚአብሄር መንፈስ ይመራው እና ያበራው ዘንድ በመጸለይ፣ ይህ ውህደት ለማረጋገጥ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርጠለሚዮስ አንደኛ የሚሰጡት አስተዋጽዖ ከፍተኛ ታማኝነት ያለው ነው ብለዋል።

በእሳቸው አማክኝነት እግዚአብሔር የሰጠው ጸጋ በዚህ በ70ኛው የልደት ዓመት ምክንያት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት የሆነው እግዚአብሔርን ለማመስገን እና በሳቸው አማክኝነት ለሕዝበ ክርስትያን እና ለሳቸውም እግዚአብሔር ለሚቸረው ቡራኬ ምስጋናን በማቅረብ ወንድማዊ መንፈስ በተካነው ቅርበት እንኳን ለ70ኛ የልደት ዓመት አደረሰዎት ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በቅርቡ ከብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርጠለሚዮስ አንደኝ ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት እና ውይይት ወንድማዊ መንፈስ የተካነው እንደነበር በማስታወስ፣ ለክርስትያን አንድነት በሚደረገው ጉዞ የሚያሳዩት ከፍተኛ እና አስተማማኝ ጥረት የማይቋረጥ ነው ሲሉ የሰጡት መግለጫ በዚህ አጋጣሚ በማስታወስ ምስጋናን በማቅረብ ያስተላለፉት መልእክት ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.