2010-03-01 14:32:10

ማለቂያ የሌለው የመስቀል መንገድ


የኢራቅ አናሳው ክርስትያን ማኅበረሰብ እያጋጠመው ያለው አመጽ፣ ማለቂያ የሌለው የመስቀል መንገድ ነው በማለት የሞሱል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤሚል ሺሙን ኖና መግለጣቸው የሚዘከር ሲሆን፣ በኢራቅ እንዲሁም RealAudioMP3 በህንድ ቤተ ክርስትያን እና ማኅበረ ክርስትያን ልክ እንደ ቀደምት ክርትያን የሰማእትነት አድማስ የተካነው ክርስትያናዊ ሕይወት እየኖረ መሆኑ ይነገራል።

ይኽ በተለያዩ አገሮች በማኅበረ ክርስትያን እና ቤተ ክርስትያን እየደረሰ ያለው አመጽ ርእስ በማድረግ የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ እና የቴሌቪዥን ማእከል ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ርእሰ አንቀጽ አቅርበዋል። በነዚህ ባለፉት ቀናት ዳግም ጸረ ክርስትያን አመጽ በሞሱል መታየቱ እና በቤተ ክርስትያን እና በማኅበረ ክርስትያን ላይ ያነጣጠረ ዛቻ አሁንም እየቀጠለ ነው ብለዋል።

ማኅበረ ክርስትያንም ምንም’ኳ በአገሩ ተዋህዶ በሰላም የሚኖር ጥንታዊ ማህበረሰብ ቢሆንም ቅሉ፣ አገሩን ለቆ እንዲሰደድ የሚገፋፋ አመጽ እየቀጠለ መሆኑ በማስታወስ፣ ተመሳሳዩ ችግር በህንድ በአንዳንድ የእስያ እና የአፍሪካ አገሮች የተለያዩ የሃይማኖት አክራሪያን ቡድኖች የሚቀሰቅሱት ማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ችግር እየታየ ነው ብለዋል።

ይህ ጸረ ክርስትያን እና ጸረ ቤተ ክርስትያን ያቀናው አመጽ ይገታ ዘንድ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ካለ መታከት ጥሪ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም ዘክረው፣ በተለያዩ አገሮች ማኅበረ ክርስትያን አብላጫ በነበረባቸው አገሮች አናሳ እይሆነ ነው ብለዋል። የክርስትያን ማኅበረሰብ ፍጻሜው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጻሜ የተለየ እንዳልሆነ የሚያረጋገጥ አጋጣሚ መሆኑም በመግለጥ፣ ፍትሕ እና የሃይማኖት ነጻነት ማረጋገጥ የሁሉም ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.