2010-02-28 18:27:18

ዒራቅ


በአሁኑ ወቅት ዒራቅ ላይ በአጠቃላይ የሀገሪቱ ሁኔታ አስከፊ እየሆነ መምጣቱ በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ በክርስትያኖች ላይ የሚፈጸመው የግድያ እና የማሳደድ ተግባር ትኩረት በመስጠት በተደጋጋሚ መዘገባችን አይዘነጋም።

በቅርቡ በሞሱል ከተማ ውስጥ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ስሶት ክርስትያን በገፍ መገደላቸው የከተማይቱ የክርስትያን ማኅበረ ሰብ አባላት ቤት ንብረታቸው ትተው እየተፈናቀሉ መሆናቸው እየተነገረ ነው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የዒራቅ ክርስትያኖች ሰቆቃው በቅርብ እየተከታተሉት መሆናቸው እና በነሱ ላይ እየወረደ ያለውን ግፍ እና መከራ በእጁ እንዳሳዘናቸው መገለጻቸው የቫቲካን የዜና መገናኛ ብዙኀን ያስታውቃሉ።

የሀገሪቱ የቤተክርስትን መሪዎችም በክርስትያን ማኅበረ ሰቦች ላይ እንደ ሚነገረው በየእስላም አክራሪዎች እየተፈጸ ያለውን ግድያ ማሳደድ ማፈን እና በአብያተክርስትያኖች የሚፈጸመው የማቃጠል ተግባር በማውገዝ እሳፋሪ ተግባሩ እንዲገታ ማሳሰባቸው እና መማጸናቸው አልቀረም የሚሰማ ጆሮ ግን እንዳልተገኘ ነው የሚነገረው።

ትናትና የቫቲካን የሃይማኖት እና ፖሊቲካ ጋዜጣ ሎሰርቫቶረ ሮማኖ ከሁለት ዓመታት በፊት የዒራቅ ጠላይ ሚኒስትር ሐሰን አል ማሊቂ ቫቲካን በጐበኙበት ግዜ የዒራቅ ክርስትያን ማኅበረሰብ አስከፊ ሁኔታ እና መፍትሔ በተመከተ በስፊው ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት እና ከሌሎች የቅድስት መንበር የበላይ ሐላፊዎች ጋር ያደረጉት ውይይት እና የሐሳብ መለዋወጥ ጠቅሶ ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ማሊቂ የክርስትያኖች ሰብአዊ እና የእምነት መሰረታዊ መብታቸው ለማስጠበቅ ቃል መግባታቸው አስታውሰዋል።

በዒራቅ የክርስትያን ማኅበረሰብ ሁኔታ ባለ መሻሻሉ እና አስከፊ እየሆነ በመሄዱ የተነሳ ባለፈው ጥር ወር መጀመርያ ሳምንት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዋና ጽሐፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ማሊቂ የዒራቅ ክርስትያን መብት እንዲጠበቅ መልእክት ማስተላለፋቸው የማይዘነጋ ነው።

ይህ በዚህ እንዳለ በዒራቅ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ እሲሲ ቻሊካት ትናትና ባቅዳድ ላይ እንደገለጡት የዒራቅ ክርስትያኖች ለማውደም የሚፈልግ የዒራቅ ታሪክን ያወድማል ማለታቸው ከባቅዳድ ተመልክተዋል።

በማያያዝም ከሁለት ሺ ዓመታት በላይ ዒራቅ ውስጥ በሰላም የኖሩ ክርስትያኖች ለማጥፋት ወይም ለማባረር እየተካሄደ ያከው እሳቸው እንዳሉት እኩይ ተግባር በምንም ዓይነት ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም።

ለዓመታት ሳይሆን ከጥንት ከዘመናት ጀምረው ከሀገሪቱ ኢስላም ኅብረተ ሰቦች በሰላም የኖሩ የዒራቅ ክርስትያኖች ለመግደል ለማሰቃየት እና ለማሳደድ የተፈልገበት ምክንያት ምን እንደሆን ጥልቅ ጥናት እንደ ሚጠይቅ ያመልከቱት በዒራቅ የቅድስት መንበር ሐዋርያው ወኪል ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ አሲሲ ቻሊካት አስከፊ ተግባሩ በቅጽበት እንዲገታ መጠየቃቸው ተገልጸዋል።

ዒራቅ ውስጥ በተለያዩ ዓበይት እና ውሁዳን ማኅበረ ሰቦች መካከል ዕርቅ እና ሰላም እንዲገኝ ብሔራዊ ድርድር እንዲደረግ እና ፍትሐዊ ሰላማዊ እና ዲሞክራስያዊ መፍትሔ እንዲከሰት በዒራቅ የቫቲካን ሐዋርያዊ ወኪል አጽንኦት ሰጥተው ማሳሰባቸው ከባቅዳድ የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

ዓለም አቀፍ ማኅበረ ሰብ በዒራቅ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እንዲተባበር የዒራቅ ውሁዳን ማኅበረ ሰቦች መብቶች ለማስከበር በዒራቅ መንግስት ላይ ተፅዕኖ እንድያሳርፍም መጠየቃቸው ተገልጠዋል። የዒራቅ መንግስት በሞሱል ከተማ እና አከባቢ በክርስትያኖች ላይ የተፈጸመው ግድያ አጣሪ ኮሚስዮን ማቋቋሙ ይህ ከባቅዳድ የድረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

ዘግይቶ የድረሰ ዜና እንዳመለከተው፡ በሞሱል ከተማ እና አከባቢ የሚኖሩ ክርስትያኖች ቤት ንብረታቸው ትተው አከባቢውን እየለቀቁ ነው።

ዒራቅ ሱኒ ሺዒቲ እና ኩርድ የተሰየሙ ዓበይት ማኅበረ ሰቦች የሚኖሩባት እንድሆነች የሚታውወስ ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.